27 “በምድሪቱ ላይ ምልክት አቁሙ።+
በብሔራት መካከል ቀንደ መለከት ንፉ።
በእሷ ላይ እንዲዘምቱ ብሔራትን መድቡ።
የአራራት፣+ የሚኒ እና የአሽከናዝ መንግሥታት+ እሷን እንዲወጉ ሰብስቧቸው።
በላይዋም ወታደሮችን የሚመለምል መኮንን ሹሙባት።
ፈረሶችንም እንደ ኩብኩባ ስደዱባት።
28 ብሔራትን፣ የሜዶንን+ ነገሥታት፣ ገዢዎቿን፣ የበታች ገዢዎቿን ሁሉና
በእያንዳንዳቸው ግዛት ሥር ያለውን ምድር ሁሉ
በእሷ ላይ እንዲዘምቱ መድቧቸው።