የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኤርምያስ 5:31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤+

      ካህናቱም በራሳቸው ሥልጣን በኃይል ይገዛሉ።

      የገዛ ሕዝቤም ይህን ወዶታል።+

      ይሁንና መጨረሻው ሲመጣ ምን ታደርጉ ይሆን?”

  • ኤርምያስ 6:12-15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ቤቶቻቸው፣ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸው

      ለሌሎች ይሰጣሉ።+

      እጄን በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ እዘረጋለሁና” ይላል ይሖዋ።

      13 “ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ እያንዳንዱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣል፤+

      ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+

      14 ሰላም ሳይኖር፣

      ‘ሰላም ነው! ሰላም ነው!’ እያሉ

      የሕዝቤን ስብራት* ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+

      15 በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል?

      እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም!

      ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+

      ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ።

      እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ” ይላል ይሖዋ።

  • ኤርምያስ 27:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 “‘“‘ስለዚህ “የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም” የሚሏችሁን በመካከላችሁ ያሉትን ነቢያት፣ ሟርተኞች፣ ሕልም አላሚዎች፣ አስማተኞችና መተተኞች አትስሙ።

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 2:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ነቢያትሽ ያዩልሽ ራእይ ሐሰትና ከንቱ ነው፤+

      ተማርከሽ እንዳትወሰጂ ለማድረግ በደልሽን አላጋለጡም፤+

      ይልቁንም ራእይ ተገለጠልን እያሉ ሐሰትና አሳሳች ቃል ይነግሩሻል።+

  • ሕዝቅኤል 22:28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 28 ነቢያቷ ግን እነሱ የሚያደርጉትን ነገር በኖራ ይለስናሉ። የሐሰት ራእዮች ያያሉ፤ የውሸት ሟርትም ያሟርታሉ፤+ ደግሞም ይሖዋ ራሱ ምንም ሳይናገር “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል” ይላሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ