ዘዳግም 28:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 አንዲትን ሴት ታጫለህ፤ ሆኖም ሌላ ሰው ይደፍራታል። ቤት ትሠራለህ፤ ሆኖም አትኖርበትም።+ ወይን ትተክላለህ፤ ግን አትበላውም።+ ኤርምያስ 8:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች ሰዎች፣እርሻዎቻቸውንም ለሌሎች እሰጣለሁ፤+ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣልና፤+ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 5:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በጽዮን ያሉ ሚስቶችና በይሁዳ ከተሞች ያሉ ደናግል ተዋረዱ።*+ ሶፎንያስ 1:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይወድማሉ።+ ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሆኖም አይኖሩባቸውም፤ወይንም ይተክላሉ፤ ሆኖም የወይን ጠጁን አይጠጡም።+
10 ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች ሰዎች፣እርሻዎቻቸውንም ለሌሎች እሰጣለሁ፤+ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣልና፤+ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+