የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 30:1-3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+ 2 እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ+ 3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+

  • ኤርምያስ 3:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 “በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት አብረው ይሄዳሉ፤+ በአንድነት ከሰሜን ምድር ተነስተው ለአባቶቻችሁ ርስት አድርጌ ወደሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።+

  • ኤርምያስ 24:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 መልካም ነገር አደርግላቸው ዘንድ ዓይኔን በእነሱ ላይ አኖራለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ።+ እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።+

  • ኤርምያስ 30:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 “እነሆ፣ ተማርከው የተወሰዱትን ሕዝቤን፣ እስራኤልንና ይሁዳን የምሰበስብበት ጊዜ ይመጣል”+ ይላል ይሖዋ፤ “ደግሞም ለአባቶቻቸው ወደሰጠኋት ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም ዳግመኛ ይወርሷታል” ይላል ይሖዋ።’”+

  • ኤርምያስ 32:37
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 37 ‘እነሆ፣ እነሱን በመዓቴና በታላቅ ቁጣዬ ከበተንኩባቸው አገሮች ሁሉ አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤+ ወደዚህም ቦታ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ ያለስጋት እንዲኖሩም አደርጋለሁ።+

  • አሞጽ 9:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+

      እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+

      የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+

      አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ