ዕዝራ 2:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ባቢሎን በግዞት ወስዷቸው+ የነበሩትና ተማርከው በግዞት ከተወሰዱት+ መካከል ወጥተው በኋላ ላይ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ይኸውም ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት የአውራጃው ነዋሪዎች እነዚህ ናቸው፤+ ኤርምያስ 29:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እኔም እገኝላችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በምርኮ የተወሰዱትን ወገኖቻችሁን እሰበስባለሁ፤ እናንተን ከበተንኩባቸው ብሔራትና ቦታዎች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በግዞት እንድትወሰዱ ባደረግኩ ጊዜ ትታችሁት ወደሄዳችሁት ቦታ መልሼ አመጣችኋለሁ።’+ ኤርምያስ 32:44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 44 “‘ተማርከው የተወሰዱባቸውን ሰዎች መልሼ ስለማመጣቸው፣+ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎች፣ በይሁዳ ከተሞች፣+ በተራራማው ምድር ባሉ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ ባሉ ከተሞችና+ በደቡብ በሚገኙ ከተሞች መሬት በገንዘብ ይገዛል፤ የግዢ ውል ተዘጋጅቶ በማኅተም ይታሸጋል፤ ምሥክሮችም ይጠራሉ’+ ይላል ይሖዋ።” ሕዝቅኤል 20:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 “‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት ወደማልኩላቸው አገር፣ ወደ እስራኤል ምድር ሳመጣችሁ+ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።+ አሞጽ 9:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+
2 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ባቢሎን በግዞት ወስዷቸው+ የነበሩትና ተማርከው በግዞት ከተወሰዱት+ መካከል ወጥተው በኋላ ላይ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ይኸውም ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት የአውራጃው ነዋሪዎች እነዚህ ናቸው፤+
14 እኔም እገኝላችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በምርኮ የተወሰዱትን ወገኖቻችሁን እሰበስባለሁ፤ እናንተን ከበተንኩባቸው ብሔራትና ቦታዎች ሁሉ እሰበስባችኋለሁ’+ ይላል ይሖዋ። ‘በግዞት እንድትወሰዱ ባደረግኩ ጊዜ ትታችሁት ወደሄዳችሁት ቦታ መልሼ አመጣችኋለሁ።’+
44 “‘ተማርከው የተወሰዱባቸውን ሰዎች መልሼ ስለማመጣቸው፣+ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎች፣ በይሁዳ ከተሞች፣+ በተራራማው ምድር ባሉ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ ባሉ ከተሞችና+ በደቡብ በሚገኙ ከተሞች መሬት በገንዘብ ይገዛል፤ የግዢ ውል ተዘጋጅቶ በማኅተም ይታሸጋል፤ ምሥክሮችም ይጠራሉ’+ ይላል ይሖዋ።”
14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+