የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ነገሥት 21:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 ምናሴ፣ ይሁዳ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም ኃጢአት እንዲሠራ በማድረግ ከሠራው ኃጢአት በተጨማሪ ኢየሩሳሌም ከዳር እስከ ዳር በደም እስክትሞላ ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደም አፍስሷል።+

  • ኢሳይያስ 59:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 እግሮቻቸው ክፋት ለመፈጸም ይሮጣሉ፤

      ንጹሕ ደም ለማፍሰስም ይጣደፋሉ።+

      የሚያስቡት ጎጂ ሐሳብ ነው፤

      በመንገዳቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ።+

  • ኤርምያስ 2:34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 ልብሶችሽ በንጹሐን ድሆች* ደም ቆሽሸዋል፤+

      ይሁንና ይህን ያገኘሁት ቤት ሲዘረፍ አይደለም፤

      ይልቁንም በልብሶችሽ ሁሉ ላይ ነው።+

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤+

      እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል።+

  • ማቴዎስ 23:34, 35
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 34 ስለዚህ ነቢያትን፣+ ጥበበኞችንና የሕዝብ አስተማሪዎችን+ ወደ እናንተ እልካለሁ። ከእነሱም መካከል አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ+ እንዲሁም በእንጨት ላይ ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በምኩራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፤+ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዷቸዋላችሁ፤+ 35 በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም+ ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ ለፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ ተጠያቂ ትሆናላችሁ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ