-
2 ነገሥት 24:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹ ከተማዋን ከበው ሳሉ ወደ ከተማዋ መጣ።
-
-
2 ዜና መዋዕል 36:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 ናቡከደነጾርም በይሖዋ ቤት ያሉ የተወሰኑ ዕቃዎችን ወደ ባቢሎን ወስዶ በባቢሎን በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ አስቀመጣቸው።+
-
-
ኤርምያስ 28:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
28 በዚያው ዓመት፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ+ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ፣ በአራተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ የገባኦን+ ሰው የሆነው የአዙር ልጅ ነቢዩ ሃናንያህ፣ በይሖዋ ቤት ውስጥ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦ 2 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁ።+ 3 በሁለት ዓመት* ጊዜ ውስጥ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ከዚህ ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የይሖዋን ቤት ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ቦታ መልሼ አመጣለሁ።’”+
-