-
ዘዳግም 30:1-4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 “ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን+ በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር+ ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት* ጊዜ+ 2 እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ*+ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ+ 3 አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤+ ምሕረትም ያሳይሃል፤+ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል።+ 4 ሕዝብህ እስከ ሰማያት ዳርቻ ድረስ ቢበተን እንኳ አምላክህ ይሖዋ ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም መልሶ ያመጣሃል።+
-