የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 26:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 በመሆኑም የወንድ ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴት ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።+

  • ዘዳግም 28:53-57
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 53  ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በአንተ ላይ ከሚያደርሰው ሥቃይ የተነሳ አምላክህ ይሖዋ የሰጠህን የሆድህን ፍሬ ይኸውም የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።+

      54 “ሌላው ቀርቶ በመካከልህ ያለ በምቾትና በቅምጥልነት ይኖር የነበረ ሰው እንኳ በወንድሙ፣ በሚወዳት ሚስቱ ወይም በተረፉት ልጆቹ ላይ ይጨክናል፤ 55 ከሚበላው የልጆቹ ሥጋ ላይ ምንም ነገር አያካፍላቸውም፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ የሚተርፈው ምንም ነገር አይኖረውም።+ 56 ከቅምጥልነቷ የተነሳ መሬት ለመርገጥ እንኳ ትጸየፍ የነበረች+ በመካከልህ ያለች ቅምጥልና በምቾት የምትኖር ሴትም በምትወደው ባሏ፣ በወንድ ልጇ ወይም በሴት ልጇ ላይ ትጨክናለች፤ 57  ሌላው ቀርቶ ከወሊድ በኋላ ከእግሮቿ መካከል በሚወጣው ነገር ሁሉና በምትወልዳቸው ልጆች ላይ ትጨክናለች፤ ምክንያቱም ከሚያስጨንቀው ከበባና ጠላትህ በከተሞችህ ላይ ከሚያመጣው ሥቃይ የተነሳ በድብቅ ትበላቸዋለች።

  • ኢዮብ 39:14-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 እንቁላሎቿን መሬት ላይ ትጥላለች፤

      በአፈርም ውስጥ ታሞቃቸዋለች።

      15 እግር ሊሰብራቸው፣

      የዱር አውሬም ሊረግጣቸው እንደሚችል አታስብም።

      16 ልጆቿ የራሷ ያልሆኑ ይመስል ትጨክንባቸዋለች፤+

      ድካሜ ሁሉ ከንቱ ይሆናል የሚል ስጋት አያድርባትም።

  • ኤርምያስ 19:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 ጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ* ሰዎች ሲከቧቸውና መፈናፈኛ አሳጥተው ሲያስጨንቋቸው የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸው የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።”’+

  • ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ሩኅሩኅ የሆኑ ሴቶች በገዛ እጃቸው ልጆቻቸውን ቀቅለዋል።+

      የሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት በደረሰባት ጊዜ እንደ እዝን እንጀራ ሆነውላቸዋል።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ