ዘዳግም 28:49, 50 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ 50 ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው።+ ኢሳይያስ 5:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 በሩቅ ላለ ታላቅ ሕዝብም ምልክት* አቁሟል፤+ከምድር ዳርቻ እንዲመጡ በፉጨት ጠርቷቸዋል፤+እነሆም፣ ሕዝቡ በከፍተኛ ፍጥነት እየመጣ ነው።+ ኤርምያስ 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እነሆ፣ እሱ ዝናብ እንዳዘሉ ደመናት ይመጣል፤ሠረገሎቹም እንደ አውሎ ነፋስ ናቸው።+ ፈረሶቹ ከንስር ይበልጥ ፈጣኖች ናቸው።+ ጠፍተናልና ወዮልን! ዕንባቆም 1:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፤ከሌሊት ተኩላዎችም ይልቅ ጨካኞች ናቸው።+ የጦር ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ፈረሶቻቸው ከሩቅ ስፍራ ይመጣሉ። ለመብላት እንደሚጣደፍ ንስር ተምዘግዝገው ይወርዳሉ።+
49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ 50 ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው።+
8 ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፤ከሌሊት ተኩላዎችም ይልቅ ጨካኞች ናቸው።+ የጦር ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ፈረሶቻቸው ከሩቅ ስፍራ ይመጣሉ። ለመብላት እንደሚጣደፍ ንስር ተምዘግዝገው ይወርዳሉ።+