12 “‘ይሁንና ሰባው ዓመት ሲፈጸም+ በበደላቸው የተነሳ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ብሔር ተጠያቂ አደርጋለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘የከለዳውያንንም ምድር እስከ ወዲያኛው ባድማ አደርገዋለሁ።+ 13 በምድሪቱ ላይ የተናገርኩትን ቃል ሁሉ ይኸውም ኤርምያስ በሁሉም ብሔራት ላይ የተነበየውንና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ነገር ሁሉ አመጣባታለሁ። 14 ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት+ ባሪያዎች ያደርጓቸዋልና፤+ እኔም እንደ ድርጊታቸውና እንደ ገዛ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።’”+