ዘፀአት 14:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እኔም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤+ እሱም ያሳድዳቸዋል፤ እኔም ፈርዖንንና ሠራዊቱን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ፤+ ግብፃውያንም እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”+ እነሱም ልክ እንዲሁ አደረጉ። 2 ነገሥት 19:17-19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ይሖዋ ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን ብሔራትና ምድራቸውን እንዳጠፉ አይካድም።+ 18 አማልክታቸውንም እሳት ውስጥ ጨምረዋል፤ ምክንያቱም የሰው እጅ ሥራ፣+ እንጨትና ድንጋይ እንጂ አማልክት አይደሉም።+ ሊያጠፏቸው የቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። 19 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ፣ አንተ ብቻ አምላክ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ከእጁ አድነን።”+ መዝሙር 83:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ሕዝቅኤል 39:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “‘በብሔራት መካከል ክብሬን እገልጣለሁ፤ ብሔራት ሁሉ የወሰድኩትን የፍርድ እርምጃና በእነሱ መካከል የገለጥኩትን ኃይል* ያያሉ።+ ኢዩኤል 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ብሔራትን ሁሉ ሰብስቤወደ ኢዮሳፍጥ* ሸለቆ* አወርዳቸዋለሁ። ለሕዝቤና ርስቴ ለሆነው ለእስራኤል ስልበዚያ ከእነሱ ጋር እፋረዳለሁ፤+በብሔራት መካከል በትነዋቸዋልና፤ደግሞም ምድሬን ተከፋፍለዋታል።+
4 እኔም የፈርዖን ልብ እንዲደነድን እፈቅዳለሁ፤+ እሱም ያሳድዳቸዋል፤ እኔም ፈርዖንንና ሠራዊቱን ድል በማድረግ ለራሴ ክብርን እጎናጸፋለሁ፤+ ግብፃውያንም እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”+ እነሱም ልክ እንዲሁ አደረጉ።
17 ይሖዋ ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ሌሎቹን ብሔራትና ምድራቸውን እንዳጠፉ አይካድም።+ 18 አማልክታቸውንም እሳት ውስጥ ጨምረዋል፤ ምክንያቱም የሰው እጅ ሥራ፣+ እንጨትና ድንጋይ እንጂ አማልክት አይደሉም።+ ሊያጠፏቸው የቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። 19 አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ፣ አንተ ብቻ አምላክ እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ከእጁ አድነን።”+
2 ብሔራትን ሁሉ ሰብስቤወደ ኢዮሳፍጥ* ሸለቆ* አወርዳቸዋለሁ። ለሕዝቤና ርስቴ ለሆነው ለእስራኤል ስልበዚያ ከእነሱ ጋር እፋረዳለሁ፤+በብሔራት መካከል በትነዋቸዋልና፤ደግሞም ምድሬን ተከፋፍለዋታል።+