6 “የሌዊን ነገድ+ አምጥተህ በካህኑ በአሮን ፊት አቁመው፤ እነሱም ያገልግሉት።+ 7 ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ የሚያከናውኑትን አገልግሎት በመፈጸም ለእሱም ሆነ ለመላው ማኅበረሰብ ያለባቸውን ኃላፊነት በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ይወጡ። 8 የመገናኛ ድንኳኑን ዕቃዎች በሙሉ በኃላፊነት መቆጣጠርና+ ከማደሪያ ድንኳኑ ጋር የተያያዘውን አገልግሎት በማከናወን ለእስራኤል ልጆች ያለባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል።+