10 ይህ ለካህናቱ መዋጮ ሆኖ የሚሰጥ ቅዱስ ስፍራ ይሆናል።+ በሰሜን በኩል 25,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 10,000፣ በምሥራቅ በኩል 10,000፣ በደቡብ በኩል ደግሞ 25,000 ይሆናል። የይሖዋ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። 11 ይህ የሳዶቅ ልጆች+ ለሆኑት የተቀደሱ ካህናት ይሆናል፤ እነሱ በእኔ ፊት ያለባቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንና ሌዋውያን በባዘኑ ጊዜ+ ከእነሱ ጋር አልባዘኑም።