የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 80:14-16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ እባክህ ተመለስ።

      ከሰማይ ወደ ታች እይ፤ ተመልከትም!

      ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤+

      15 ቀኝ እጅህ የተከላትን ግንድ*+ በእንክብካቤ ያዛት፤

      ለራስህ ስትል ያጠነከርከውንም ልጅ* ተመልከት።+

      16 እሷ ተቆርጣ በእሳት ተቃጥላለች።+

      ሕዝቡ ከተግሣጽህ* የተነሳ ይጠፋል።

  • ኢሳይያስ 5:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣

      የደረቀም ሣር በነበልባል በንኖ እንደሚጠፋ

      የእነሱም ሥር ይበሰብሳል፤

      አበባቸውም ልክ እንደ ዱቄት በየቦታው ይበናል፤

      ምክንያቱም እነሱ የሠራዊት ጌታ የሆነውን የይሖዋን ሕግ* ለመቀበል አሻፈረን ብለዋል፣

      የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል ንቀዋል።+

  • ኤርምያስ 7:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤+ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’+

  • ሕዝቅኤል 20:47
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 47 በደቡብ ለሚገኘው ደን እንዲህ በል፦ ‘የይሖዋን ቃል ስማ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንተ ላይ እሳት አነዳለሁ፤+ እሳቱም በአንተ ውስጥ ያለውን የለመለመውንና ደረቁን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንቦገቦገው ነበልባል አይጠፋም፤+ እሱም ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት* ሁሉ ይለበልባል።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ