25 “የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አሁን ትኩረቴን በኖእ+ ከተማ ወደሚገኘው ወደ አምዖን፣+ ወደ ፈርዖን፣ ወደ ግብፅ፣ ወደ አማልክቷና+ ወደ ነገሥታቷ፣ አዎ በፈርዖንና በእሱ ወደሚታመኑት ሰዎች ሁሉ አደርጋለሁ።’+
26 “‘ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚሹ ሰዎች፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾርና ለአገልጋዮቹ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።+ ከዚያ በኋላ ግን እንደቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች’ ይላል ይሖዋ።+