14 ከዚያም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ እስራኤላውያን በሰባተኛው ወር በሚከበረው በዓል ወቅት ዳስ+ ውስጥ መቀመጥ እንዳለባቸው የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ፤ 15 እንዲሁም “ወደ ተራራማው አካባቢ ውጡና በተጻፈው መሠረት ዳሶችን ለመሥራት ከወይራ ዛፍ፣ ከዘይት ዛፍ፣ ከአደስ ዛፍ፣ ከዘንባባና ከሌሎች ዛፎች ቅጠል ያላቸውን ቅርንጫፎች አምጡ” የሚል አዋጅ በከተሞቻቸው በሙሉና በመላው ኢየሩሳሌም ማወጅ እንዳለባቸው+ የሚገልጽ ሐሳብ ተጽፎ አገኙ።