-
1 ነገሥት 17:20-23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 እሱም “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣+ እኔን ያሳረፈችኝ የዚህች መበለት ልጅ እንዲሞት በማድረግ በእሷም ላይ መከራ ታመጣባታለህ?” በማለት ወደ ይሖዋ ጮኸ። 21 ከዚያም ልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ከተዘረጋበት በኋላ “አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ የዚህ ልጅ ሕይወት ይመለስለት”* ብሎ ወደ ይሖዋ ጮኸ። 22 ይሖዋም የኤልያስን ልመና ሰማ፤+ የልጁም ሕይወት ተመለሰለት፤* እሱም ሕያው ሆነ።+ 23 ከዚያም ኤልያስ ልጁን ይዞት ሰገነት ላይ ካለው ክፍል ወደ ቤት ከወረደ በኋላ ለእናቱ ሰጣት፤ ኤልያስም “ይኸው፣ ልጅሽ ሕያው ሆኗል” አላት።+
-
-
2 ነገሥት 4:13-17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ከዚያም ኤልሳዕ ግያዝን እንዲህ አለው፦ “እባክህ እንዲህ በላት፦ ‘እንግዲህ ለእኛ ስትዪ ብዙ ተቸግረሻል።+ ታዲያ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊያለሽ?+ ንጉሡን ወይም የሠራዊቱን አለቃ የማነጋግርልሽ ነገር አለ?’”+ እሷ ግን “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” ብላ መለሰች። 14 እሱም “ታዲያ ምን ቢደረግላት ይሻላል?” አለ። ግያዝም “ለነገሩማ ሴትየዋ ወንድ ልጅ የላትም፤+ ባሏ ደግሞ አርጅቷል” አለው። 15 ኤልሳዕም ወዲያውኑ “በል ጥራት” አለው። እሱም ጠራት፤ እሷም በራፉ ላይ ቆመች። 16 ከዚያም “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት።+ እሷ ግን “የእውነተኛው አምላክ ሰው ጌታዬ ሆይ፣ ይሄማ አይሆንም! አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ” አለችው።
17 ይሁንና ሴትየዋ ፀነሰች፤ ኤልሳዕ በነገራትም መሠረት በቀጣዩ ዓመት በዚያው ጊዜ ወንድ ልጅ ወለደች።
-