-
ማርቆስ 14:37-42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
37 ተመልሶ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸውና ጴጥሮስን እንዲህ አለው፦ “ስምዖን፣ ተኝተሃል? አንድ ሰዓት እንኳ ነቅተህ መጠበቅ አልቻልክም?+ 38 ወደ ፈተና እንዳትገቡ+ ነቅታችሁ ጠብቁ፤ ሳታሰልሱም ጸልዩ። እርግጥ፣ መንፈስ ዝግጁ* ነው፤ ሥጋ* ግን ደካማ ነው።”+ 39 እንደገናም ሄዶ ስለዚያው ነገር ጸለየ።+ 40 ዳግመኛም ተመልሶ ሲመጣ እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ስለነበር ተኝተው አገኛቸው፤ በመሆኑም የሚሉት ነገር ጠፋቸው። 41 ለሦስተኛ ጊዜም ተመልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የእንቅልፍና የእረፍት ሰዓት ነው? በቃ! ሰዓቱ ደርሷል!+ እነሆ፣ የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ ሊሰጥ ነው። 42 ተነሱ፣ እንሂድ። እነሆ፣ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል።”+
-
-
ሉቃስ 22:45አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
45 ከጸለየም በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲሄድ ከሐዘን የተነሳ ደክሟቸው ስለነበር ሲያንቀላፉ አገኛቸው።+
-