የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማርቆስ 14:66-72
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 66 ጴጥሮስ ግቢው ውስጥ በታች በኩል ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ሴት አገልጋዮች አንዷ መጣች።+ 67 እሳት ሲሞቅ አይታ ትኩር ብላ ተመለከተችውና “አንተም ከዚህ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርክ” አለችው። 68 እሱ ግን “ሰውየውን አላውቀውም፤ ምን እንደምታወሪም አላውቅም” ሲል ካደ፤ ከዚያም ወደ መግቢያው* ሄደ። 69 አገልጋይዋም እዚያ አየችውና በአጠገቡ ለቆሙት “ይህ ከእነሱ አንዱ ነው” ብላ እንደገና ትናገር ጀመር። 70 አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ በዚያ ቆመው የነበሩት ጴጥሮስን እንደገና “የገሊላ ሰው ስለሆንክ፣ በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” ይሉት ጀመር። 71 እሱ ግን “ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም!” ሲል ይምልና ራሱን ይረግም ጀመር። 72 ወዲያውኑ ዶሮ ለሁለተኛ ጊዜ ጮኸ፤+ ጴጥሮስም “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለው።+ ከዚያም እጅግ አዝኖ ያለቅስ ጀመር።

  • ሉቃስ 22:54-62
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 54 ከዚያም ሰዎቹ ይዘው ወሰዱትና+ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት አመጡት፤ ጴጥሮስም በርቀት ይከተል ነበር።+ 55 በግቢው መካከል እሳት አንድደው አንድ ላይ ተቀምጠው ሳለ ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ተቀመጠ።+ 56 ይሁንና አንዲት አገልጋይ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሲሞቅ አየችውና ትኩር ብላ ከተመለከተችው በኋላ “ይህ ሰውም ከእሱ ጋር ነበር” አለች። 57  እሱ ግን “አንቺ ሴት፣ እኔ አላውቀውም” ሲል ካደ። 58 ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው አየውና “አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ አይደለሁም” አለ።+ 59 አንድ ሰዓት ያህል ካለፈ በኋላ ደግሞ አንድ ሌላ ሰው “ይህ ሰው፣ የገሊላ ሰው ስለሆነ በእርግጥ ከእሱ ጋር ነበር!” በማለት አጥብቆ ይናገር ጀመር። 60 ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ ምን እንደምታወራ አላውቅም” አለ። ገና እየተናገረም ሳለ ዶሮ ጮኸ። 61 በዚህ ጊዜ ጌታ ዞር ብሎ ጴጥሮስን ትክ ብሎ አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ የተናገረውን ቃል አስታወሰ።+ 62 ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።

  • ዮሐንስ 18:15-17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ስምዖን ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን እየተከተሉ ነበር።+ ይህን ደቀ መዝሙር ሊቀ ካህናቱ ያውቀው ስለነበር ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ገባ፤ 16 ጴጥሮስ ግን ውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር። ስለሆነም ሊቀ ካህናቱ የሚያውቀው ይህ ደቀ መዝሙር ወጥቶ በር ጠባቂዋን አነጋገራትና ጴጥሮስን አስገባው። 17 በር ጠባቂ የነበረችውም አገልጋይ ጴጥሮስን “አንተም ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አለችው። እሱም “አይደለሁም” አለ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ