የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 26:69-75
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 69 ጴጥሮስ ከቤት ውጭ፣ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ወደ እሱ መጥታ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርክ!” አለችው።+ 70 እሱ ግን “ስለ ምን እየተናገርሽ እንዳለ አላውቅም” በማለት በሁሉም ፊት ካደ። 71 ወደ ግቢው መግቢያ አካባቢ ሲሄድ ሌላ ሴት አየችውና በዚያ ለነበሩት ሰዎች “ይህ ሰው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበር” አለች።+ 72 እሱም “ሰውየውን አላውቀውም!” ብሎ በመማል ዳግመኛ ካደ። 73 ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካባቢው ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን “አነጋገርህ* ያስታውቃል፤ በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አሉት። 74 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ሰውየውን አላውቀውም!” በማለት ይምልና ራሱን ይረግም ጀመር። ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ። 75 ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”+ ሲል ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።

  • ማርቆስ 14:66-72
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 66 ጴጥሮስ ግቢው ውስጥ በታች በኩል ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ሴት አገልጋዮች አንዷ መጣች።+ 67 እሳት ሲሞቅ አይታ ትኩር ብላ ተመለከተችውና “አንተም ከዚህ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርክ” አለችው። 68 እሱ ግን “ሰውየውን አላውቀውም፤ ምን እንደምታወሪም አላውቅም” ሲል ካደ፤ ከዚያም ወደ መግቢያው* ሄደ። 69 አገልጋይዋም እዚያ አየችውና በአጠገቡ ለቆሙት “ይህ ከእነሱ አንዱ ነው” ብላ እንደገና ትናገር ጀመር። 70 አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ በዚያ ቆመው የነበሩት ጴጥሮስን እንደገና “የገሊላ ሰው ስለሆንክ፣ በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” ይሉት ጀመር። 71 እሱ ግን “ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም!” ሲል ይምልና ራሱን ይረግም ጀመር። 72 ወዲያውኑ ዶሮ ለሁለተኛ ጊዜ ጮኸ፤+ ጴጥሮስም “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለው።+ ከዚያም እጅግ አዝኖ ያለቅስ ጀመር።

  • ዮሐንስ 18:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 ብርድ ስለነበር ባሪያዎቹና የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ባቀጣጠሉት ከሰል ዙሪያ ቆመው እየሞቁ ነበር። ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ