የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 14:15-21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ ቀርበው “ቦታው ገለል ያለ ነው፤ ሰዓቱ ደግሞ ገፍቷል፤ ስለዚህ ሕዝቡ ወደ መንደሮቹ ሄደው ምግብ እንዲገዙ አሰናብታቸው” አሉት።+ 16 ይሁን እንጂ ኢየሱስ “መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። 17 እነሱም “ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ በስተቀር እዚህ ምንም ነገር የለንም” አሉት። 18 እሱም “ያለውን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው። 19 ሕዝቡንም ሣሩ ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ከዚያም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ፤+ ዳቦውን ከቆረሰ በኋላም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ እነሱ ደግሞ ለሕዝቡ ሰጡ። 20 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ 21 የበሉትም ከሴቶችና ከትናንሽ ልጆች ሌላ 5,000 ወንዶች ነበሩ።+

  • ሉቃስ 9:12-17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 ቀኑም መምሸት ሲጀምር አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ወደ እሱ መጥተው “ያለንበት ስፍራ ገለል ያለ ስለሆነ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት።+ 13 እሱ ግን “እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው።+ እነሱም “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ምግብ ካልገዛን በስተቀር ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ ሌላ ምንም የለንም” አሉት። 14 በዚያም 5,000 ያህል ወንዶች ነበሩ። እሱ ግን ደቀ መዛሙርቱን “ሕዝቡን በሃምሳ በሃምሳ ከፋፍላችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው። 15 እነሱም በታዘዙት መሠረት ሕዝቡ እንዲቀመጥ አደረጉ። 16 ከዚያም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ። ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። 17 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ