የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 9:3-8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጸሐፍት በልባቸው “ይህ ሰው እኮ አምላክን እየተዳፈረ ነው” አሉ። 4 ኢየሱስ ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ፦ “በልባችሁ ክፉ ነገር የምታስቡት ለምንድን ነው?+ 5 ለመሆኑ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነስተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል?+ 6 ይሁን እንጂ የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .” አላቸውና ሽባውን “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።+ 7 እሱም ተነስቶ ወደ ቤቱ ሄደ። 8 ሕዝቡም ይህን ሲያዩ በፍርሃት ተዋጡ፤ እንዲህ ያለ ሥልጣን ለሰው የሰጠውንም አምላክ አከበሩ።

  • ሉቃስ 5:21-26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን “አምላክን የሚዳፈረው ይሄ ማን ነው? ከአምላክ በቀር ኃጢአትን ማን ይቅር ሊል ይችላል?” ይባባሉ ጀመር።+ 22 ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ተረድቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በልባችሁ የምታስቡት ምንድን ነው? 23 ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነስተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል? 24 ይሁንና የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .” አላቸውና ሽባውን “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።+ 25 በዚህ ጊዜ ሰውየው በፊታቸው ተነስቶ ተኝቶበት የነበረውን ቃሬዛ ተሸከመና አምላክን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ። 26 ይህን ሲያዩ ሁሉም በአድናቆት ተውጠው አምላክን ማመስገን ጀመሩ፤ ታላቅ ፍርሃትም አድሮባቸው “ዛሬ የሚያስደንቅ ነገር አየን!” አሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ