የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 21:22, 23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 “አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ሠርቶ ቢገደልና+ በእንጨት ላይ ብትሰቅለው+ 23 በድኑ በእንጨቱ ላይ አይደር።+ ከዚህ ይልቅ በዚያው ዕለት ቅበረው፤ ምክንያቱም እንጨት ላይ የሚሰቀለው፣ አምላክ የረገመው ነው፤+ አንተም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር አታርክስ።+

  • ማቴዎስ 27:57, 58
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 57  ቀኑ በመገባደድ ላይ ሳለ የአርማትያስ ሰው የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሀብታም መጣ፤ እሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር።+ 58 ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጠየቀ።+ ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።+

  • ሉቃስ 23:50-52
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 50 እነሆም፣ የሸንጎ* አባል የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ጥሩና ጻድቅ ሰው ነበረ።+ 51 (ይህ ሰው ሴራቸውንና ድርጊታቸውን በመደገፍ ድምፅ አልሰጠም ነበር።) እሱም የአይሁዳውያን ከተማ የሆነችው የአርማትያስ ሰው ሲሆን የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር። 52 ይህም ሰው ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ።

  • ዮሐንስ 19:38
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 38 ይህ ከሆነ በኋላ፣ የአርማትያሱ ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ጠየቀ፤ ዮሴፍ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር። ሆኖም አይሁዳውያንን* ይፈራ ስለነበር+ ይህን ለማንም አልተናገረም። ጲላጦስ ከፈቀደለት በኋላ መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን ወሰደ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ