33 በምኩራቡም ውስጥ ርኩስ መንፈስ ማለትም ጋኔን ያደረበት አንድ ሰው ነበር፤ ሰውየውም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦+ 34 “እንዴ! የናዝሬቱ ኢየሱስ፣+ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን? የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ።”+ 35 ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም ሰውየውን በሕዝቡ ፊት ከጣለው በኋላ ምንም ሳይጎዳው ለቆት ወጣ።