-
ማቴዎስ 11:16-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 “ይህን ትውልድ ከማን ጋር ላመሳስለው?+ በገበያ ስፍራ ተቀምጠው ጓደኞቻቸውን እየተጣሩ እንዲህ ከሚሉ ልጆች ጋር ይመሳሰላል፦ 17 ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ እናንተ ግን በሐዘን ደረታችሁን አልደቃችሁም።’ 18 በተመሳሳይም ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ ሰዎች ግን ‘ጋኔን አለበት’ አሉ። 19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤+ ሰዎች ግን ‘እዩ፣ ይህን ሆዳምና ለወይን ጠጅ ያደረ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ’ አሉ።+ የሆነ ሆኖ፣ ጥበብ ጻድቅ መሆኗ* በሥራዋ* ተረጋግጧል።”+
-