-
ማቴዎስ 26:6, 7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ኢየሱስ በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን+ ቤት ሳለ 7 አንዲት ሴት በጣም ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እሱ ቀረበች፤ እየበላ ሳለም ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር።
-
-
ማርቆስ 14:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን ቤት እየበላ ሳለ አንዲት ሴት እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች። ብልቃጡንም ሰብራ በመክፈት ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር።+
-