የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 20:29-34
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 ከኢያሪኮ ወጥተው እየሄዱ ሳሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተለው። 30 በዚህ ጊዜ መንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ዓይነ ስውሮች ኢየሱስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልን!” እያሉ ጮኹ።+ 31 ሆኖም ሕዝቡ ዝም እንዲሉ ገሠጿቸው፤ እነሱ ግን “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልን!” እያሉ ይበልጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ። 32 ኢየሱስም ቆም ብሎ ጠራቸውና “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። 33 እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ዓይናችንን አብራልን” አሉት። 34 ኢየሱስም በጣም አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ፤+ ወዲያውኑም ማየት ቻሉ፤ ከዚያም ተከተሉት።

  • ማርቆስ 10:46-52
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 46 ከዚያም ወደ ኢያሪኮ መጡ። እሱና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዓይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።+ 47 እሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ሲሰማ “የዳዊት ልጅ፣+ ኢየሱስ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!”+ እያለ ይጮኽ ጀመር። 48 በዚህ ጊዜ ብዙዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ። 49 ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። እነሱም ዓይነ ስውሩን “አይዞህ! ተነስ፤ እየጠራህ ነው” አሉት። 50 እሱም መደረቢያውን ጥሎ ዘሎ በመነሳት ወደ ኢየሱስ ሄደ። 51 ኢየሱስም “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዓይነ ስውሩም “ራቦኒ፣* የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው። 52 ኢየሱስም “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+ ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤+ እሱም ከሕዝቡ ጋር አብሮ ይከተለው ጀመር።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ