-
ማቴዎስ 9:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ ሁለት ዓይነ ስውሮች+ “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልን” ብለው እየጮኹ ተከተሉት።
-
-
ማርቆስ 10:46-52አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
46 ከዚያም ወደ ኢያሪኮ መጡ። እሱና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዓይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።+ 47 እሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ሲሰማ “የዳዊት ልጅ፣+ ኢየሱስ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!”+ እያለ ይጮኽ ጀመር። 48 በዚህ ጊዜ ብዙዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ። 49 ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። እነሱም ዓይነ ስውሩን “አይዞህ! ተነስ፤ እየጠራህ ነው” አሉት። 50 እሱም መደረቢያውን ጥሎ ዘሎ በመነሳት ወደ ኢየሱስ ሄደ። 51 ኢየሱስም “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዓይነ ስውሩም “ራቦኒ፣* የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው። 52 ኢየሱስም “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+ ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤+ እሱም ከሕዝቡ ጋር አብሮ ይከተለው ጀመር።
-
-
ሉቃስ 18:35-43አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
35 ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ እየተቃረበ ሳለ አንድ ዓይነ ስውር መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።+ 36 ዓይነ ስውሩም ብዙ ሕዝብ በዚያ ሲያልፍ ሰምቶ ስለ ሁኔታው ይጠይቅ ጀመር። 37 ሰዎቹም “የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ እያለፈ ነው!” ብለው ነገሩት። 38 በዚህ ጊዜ “ኢየሱስ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” ሲል ጮኸ። 39 ከፊት ከፊት የሚሄዱትም ሰዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ። 40 ኢየሱስም ቆመና ሰውየውን ወደ እሱ እንዲያመጡት አዘዘ። ሰውየው ወደ እሱ በቀረበ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ 41 “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” እሱም “ጌታ ሆይ፣ የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው። 42 ስለዚህ ኢየሱስ “የዓይንህ ብርሃን ይመለስልህ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።+ 43 ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤ አምላክን እያመሰገነም ይከተለው ጀመር።+ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ አምላክን አወደሱ።+
-