-
ማቴዎስ 22:23-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 በዚያኑ ዕለት፣ በትንሣኤ የማያምኑት+ ሰዱቃውያን መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦+ 24 “መምህር፣ ሙሴ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ የሟቹን ሚስት ማግባትና ለወንድሙ ዘር መተካት አለበት’ ብሏል።+ 25 በእኛ ዘንድ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ በመሞቱ ወንድሙ የሟቹን ሚስት አገባ። 26 ሁለተኛውም ሆነ ሦስተኛው እስከ ሰባተኛው ድረስ ልጅ ሳይወልዱ ሞቱ። 27 በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። 28 እንግዲህ ሁሉም ስላገቧት በትንሣኤ ከሰባቱ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?”
-
-
ማርቆስ 12:18-23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 በትንሣኤ የማያምኑት+ ሰዱቃውያን ደግሞ መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦+ 19 “መምህር፣ ሙሴ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሚስቱ በሞት ቢለይ ወንድሙ ሚስትየዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር መተካት እንዳለበት ጽፎልናል።+ 20 ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አገባና ዘር ሳይተካ ሞተ። 21 ከዚያም ሁለተኛው አገባት፤ ሆኖም ዘር ሳይተካ ሞተ፤ ሦስተኛውም እንዲሁ፤ 22 ሰባቱም ዘር አልተኩም። በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። 23 እንግዲህ ሰባቱም ስላገቧት በትንሣኤ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?”
-