8 ለአንዱ በመንፈስ አማካኝነት በጥበብ የመናገር ችሎታ ይሰጠዋልና፤ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ በእውቀት የመናገር ችሎታ ይሰጠዋል፤ 9 ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፤+ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ፣ የመፈወስ ስጦታ ይሰጠዋል፤+ 10 እንዲሁም ለሌላው ተአምራት የመሥራት፣+ ለሌላው ትንቢት የመናገር፣ ለሌላው በመንፈስ መሪነት የተነገረን ቃል የመረዳት፣+ ለሌላው በተለያዩ ልሳኖች የመናገር፣+ ለሌላው ደግሞ ልሳኖችን የመተርጎም ችሎታ ይሰጠዋል።+