የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ቆሮንቶስ 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • የምሥራቹ ብርሃን (1-6)

        • “የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል” (4)

      • በሸክላ ዕቃ ውስጥ ያለ ውድ ሀብት (7-18)

2 ቆሮንቶስ 4:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 2:17፤ ገላ 1:9
  • +2ቆሮ 6:3, 4

2 ቆሮንቶስ 4:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የዚህ ዘመን።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 1:15፤ ዕብ 1:3
  • +ኢሳ 60:2፤ ዮሐ 8:12
  • +ዮሐ 14:30፤ ኤፌ 2:2፤ 1ዮሐ 5:19
  • +2ቆሮ 11:14

2 ቆሮንቶስ 4:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 1:3
  • +1ጴጥ 2:9

2 ቆሮንቶስ 4:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 12:9, 10፤ ፊልጵ 4:13
  • +2ቆሮ 4:1
  • +ኢሳ 64:8፤ ሥራ 9:15፤ 1ቆሮ 15:47

2 ቆሮንቶስ 4:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ተስፋ አንቆርጥም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 10:13

2 ቆሮንቶስ 4:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ብንወድቅም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 13:5
  • +ራእይ 2:10

2 ቆሮንቶስ 4:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ፊልጵ 3:10፤ 1ጴጥ 4:13

2 ቆሮንቶስ 4:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 8:36፤ 1ቆሮ 4:9፤ 15:31

2 ቆሮንቶስ 4:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 116:10

2 ቆሮንቶስ 4:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 6:14

2 ቆሮንቶስ 4:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ጢሞ 2:10

2 ቆሮንቶስ 4:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፈተና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:12፤ ሮም 8:18

2 ቆሮንቶስ 4:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 5:7፤ ዕብ 11:1

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ቆሮ. 4:22ቆሮ 2:17፤ ገላ 1:9
2 ቆሮ. 4:22ቆሮ 6:3, 4
2 ቆሮ. 4:4ቆላ 1:15፤ ዕብ 1:3
2 ቆሮ. 4:4ኢሳ 60:2፤ ዮሐ 8:12
2 ቆሮ. 4:4ዮሐ 14:30፤ ኤፌ 2:2፤ 1ዮሐ 5:19
2 ቆሮ. 4:42ቆሮ 11:14
2 ቆሮ. 4:6ዘፍ 1:3
2 ቆሮ. 4:61ጴጥ 2:9
2 ቆሮ. 4:72ቆሮ 12:9, 10፤ ፊልጵ 4:13
2 ቆሮ. 4:72ቆሮ 4:1
2 ቆሮ. 4:7ኢሳ 64:8፤ ሥራ 9:15፤ 1ቆሮ 15:47
2 ቆሮ. 4:81ቆሮ 10:13
2 ቆሮ. 4:9ዕብ 13:5
2 ቆሮ. 4:9ራእይ 2:10
2 ቆሮ. 4:10ፊልጵ 3:10፤ 1ጴጥ 4:13
2 ቆሮ. 4:11ሮም 8:36፤ 1ቆሮ 4:9፤ 15:31
2 ቆሮ. 4:13መዝ 116:10
2 ቆሮ. 4:141ቆሮ 6:14
2 ቆሮ. 4:152ጢሞ 2:10
2 ቆሮ. 4:17ማቴ 5:12፤ ሮም 8:18
2 ቆሮ. 4:182ቆሮ 5:7፤ ዕብ 11:1
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ቆሮንቶስ 4:1-18

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ

4 ስለዚህ በተደረገልን ምሕረት የተነሳ ይህ አገልግሎት ስላለን ተስፋ አንቆርጥም። 2 ከዚህ ይልቅ አሳፋሪ የሆኑትን ስውር ነገሮች ትተናል፤ በተንኮል አንመላለስም፤ የአምላክንም ቃል አንበርዝም፤+ ነገር ግን እውነትን በመግለጥ በአምላክ ፊት የሰውን ሁሉ ሕሊና በሚማርክ መንገድ ራሳችንን ብቁ አድርገን እናቀርባለን።+ 3 እንግዲህ የምናውጀው ምሥራች በእርግጥ የተሸፈነ ከሆነ የተሸፈነው ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ነው፤ 4 የአምላክ አምሳል ስለሆነው ስለ ክርስቶስ+ የሚገልጸውና ክብራማ የሆነው ምሥራች የሚፈነጥቀው ብርሃን በእነሱ ላይ እንዳያበራ+ የዚህ ሥርዓት* አምላክ+ የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል።+ 5 እኛ የምንሰብከው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ስለ ኢየሱስ ስንል የእናንተ ባሪያዎች መሆናችንን እንጂ ስለ ራሳችን አይደለምና። 6 “በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይብራ” ያለው አምላክ ነውና፤+ ስለሆነም በክርስቶስ ፊት አማካኝነት፣ በልባችን ውስጥ ስለ አምላክ አስደናቂ እውቀት ይፈነጥቅ ዘንድ በልባችን ላይ ብርሃን አብርቷል።+

7 ይሁን እንጂ ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነው ኃይል ከእኛ ሳይሆን ከአምላክ የመነጨ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ+ ይህ ውድ ሀብት+ በሸክላ ዕቃ+ ውስጥ አለን። 8 በየአቅጣጫው ብንደቆስም መፈናፈኛ አናጣም፤ ግራ ብንጋባም መውጫ ቀዳዳ አናጣም፤*+ 9 ስደት ቢደርስብንም አልተተውንም፤+ በጭንቀት ብንዋጥም* አንጠፋም።+ 10 የኢየሱስ ሕይወት በእኛም ሰውነት እንዲገለጥ በኢየሱስ ላይ የደረሰውን ለሞት ሊዳርግ የሚችል መከራ ዘወትር በሰውነታችን እንሸከማለን።+ 11 የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችንም ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆን ለኢየሱስ ስንል ዘወትር ከሞት ጋር እንፋጠጣለንና።+ 12 ስለሆነም በእኛ ላይ ሞት፣ በእናንተ ላይ ግን ሕይወት እየሠራ ነው።

13 “አመንኩ፤ ስለዚህም ተናገርኩ” ተብሎ ተጽፏል።+ እኛም እንዲህ ዓይነት የእምነት መንፈስ ስላለን እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፤ 14 ኢየሱስን ያስነሳው እሱ፣ እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሳንና ከእናንተ ጋር አንድ ላይ በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን።+ 15 ይህ ሁሉ የሆነው ለእናንተ ሲባል ነውና፤ ይኸውም ብዙ ሰዎች ለአምላክ ክብር ምስጋና እያቀረቡ ስለሆነ የተትረፈረፈው ጸጋ ይበልጥ እንዲበዛ ነው።+

16 ስለዚህ ተስፋ አንቆርጥም፤ ምንም እንኳ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድም ውስጣዊው ሰውነታችን ከቀን ወደ ቀን እየታደሰ እንደሚሄድ ምንም ጥርጥር የለውም። 17 የሚደርስብን መከራ* ጊዜያዊና ቀላል ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድና ዘላለማዊ የሆነ ክብር ያስገኝልናል፤+ 18 ስለዚህ ዓይናችን እንዲያተኩር የምናደርገው በሚታዩት ነገሮች ላይ ሳይሆን በማይታዩት ነገሮች ላይ ነው።+ የሚታዩት ጊዜያዊ ናቸውና፤ የማይታዩት ግን ዘላለማዊ ናቸው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ