የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዕብራውያን 10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዕብራውያን የመጽሐፉ ይዘት

      • የእንስሳት መሥዋዕት ኃጢአትን ማስወገድ አይችልም (1-4)

        • ሕጉ ጥላ ነው (1)

      • ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የቀረበ የክርስቶስ መሥዋዕት (5-18)

      • “ወደ ሕይወት የሚመራ አዲስ መንገድ” (19-25)

        • “መሰብሰባችንን ቸል አንበል” (24, 25)

      • ሆን ብሎ በኃጢአት ጎዳና ከመመላለስ መራቅ (26-31)

      • የተስፋው ቃል ሲፈጸም ለማየት መጽናት (32-39)

ዕብራውያን 10:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ስለዚህ ሰዎች . . . ሊያደርጓቸው አይችሉም” ማለትም ሊሆን ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 2:16, 17፤ ዕብ 8:5
  • +ዕብ 7:19፤ 9:9

ዕብራውያን 10:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 16:34

ዕብራውያን 10:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 40:6

ዕብራውያን 10:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 40:8

ዕብራውያን 10:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 40:6-8

ዕብራውያን 10:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ገላ 1:4
  • +ዕብ 13:12

ዕብራውያን 10:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ሕዝባዊ አገልግሎት ለመስጠትና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 2:27, 28
  • +ዕብ 7:18፤ 10:1
  • +ዘፀ 29:38፤ ዘኁ 28:3

ዕብራውያን 10:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 8:34

ዕብራውያን 10:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 110:1፤ 1ቆሮ 15:25

ዕብራውያን 10:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 7:19

ዕብራውያን 10:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 31:33፤ ዕብ 8:10

ዕብራውያን 10:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኤር 31:34፤ ዕብ 8:12

ዕብራውያን 10:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የመተማመን ስሜት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕብ 9:8, 24

ዕብራውያን 10:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የመረቀልን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 27:51

ዕብራውያን 10:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘካ 6:13፤ ዕብ 3:6

ዕብራውያን 10:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዮሐ 1:7
  • +ኤፌ 5:25, 26

ዕብራውያን 10:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 15:58፤ ቆላ 1:23

ዕብራውያን 10:24

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አንዳችን ሌላውን ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መቀስቀስ ወይም ማነሳሳት።”

  • *

    ወይም “እናስብ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ቆላ 3:23፤ 1ጢሞ 6:18

ዕብራውያን 10:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ለአምልኮ መሰብሰብን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 31:12፤ ሥራ 2:42
  • +ኢሳ 35:3፤ ሮም 1:11, 12
  • +ሮም 13:11፤ 2ጴጥ 3:11, 12

ዕብራውያን 10:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ጴጥ 2:21
  • +ማቴ 12:32፤ ዕብ 6:4-6፤ 1ዮሐ 5:16

ዕብራውያን 10:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 26:11

ዕብራውያን 10:28

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 17:6

ዕብራውያን 10:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 26:27, 28፤ ሉቃስ 22:20
  • +ዕብ 6:4-6

ዕብራውያን 10:30

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 32:35, 36

ዕብራውያን 10:32

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 4:6፤ ዕብ 6:4

ዕብራውያን 10:33

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ቲያትር ላይ የቀረባችሁ ያህል የተጋለጣችሁባቸው።”

  • *

    ወይም “እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ከደረሰባቸው ሰዎች ጎን የቆማችሁባቸው።”

ዕብራውያን 10:34

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 16:9
  • +ማቴ 5:12

ዕብራውያን 10:35

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 10:32፤ 1ቆሮ 15:58

ዕብራውያን 10:36

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 21:19፤ ያዕ 5:11

ዕብራውያን 10:37

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢሳ 26:20
  • +ዕን 2:3፤ 2ጴጥ 3:9

ዕብራውያን 10:38

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሴ በእሱ ደስ አትሰኝም።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 3:16፤ ሮም 1:17
  • +ዕን 2:4

ዕብራውያን 10:39

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍስን ጠብቆ የሚያኖር።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ጴጥ 2:20

ተዛማጅ ሐሳብ

ዕብ. 10:1ቆላ 2:16, 17፤ ዕብ 8:5
ዕብ. 10:1ዕብ 7:19፤ 9:9
ዕብ. 10:3ዘሌ 16:34
ዕብ. 10:6መዝ 40:6
ዕብ. 10:7መዝ 40:8
ዕብ. 10:9መዝ 40:6-8
ዕብ. 10:10ገላ 1:4
ዕብ. 10:10ዕብ 13:12
ዕብ. 10:111ሳሙ 2:27, 28
ዕብ. 10:11ዕብ 7:18፤ 10:1
ዕብ. 10:11ዘፀ 29:38፤ ዘኁ 28:3
ዕብ. 10:12ሮም 8:34
ዕብ. 10:13መዝ 110:1፤ 1ቆሮ 15:25
ዕብ. 10:14ዕብ 7:19
ዕብ. 10:16ኤር 31:33፤ ዕብ 8:10
ዕብ. 10:17ኤር 31:34፤ ዕብ 8:12
ዕብ. 10:19ዕብ 9:8, 24
ዕብ. 10:20ማቴ 27:51
ዕብ. 10:21ዘካ 6:13፤ ዕብ 3:6
ዕብ. 10:221ዮሐ 1:7
ዕብ. 10:22ኤፌ 5:25, 26
ዕብ. 10:231ቆሮ 15:58፤ ቆላ 1:23
ዕብ. 10:24ቆላ 3:23፤ 1ጢሞ 6:18
ዕብ. 10:25ዘዳ 31:12፤ ሥራ 2:42
ዕብ. 10:25ኢሳ 35:3፤ ሮም 1:11, 12
ዕብ. 10:25ሮም 13:11፤ 2ጴጥ 3:11, 12
ዕብ. 10:262ጴጥ 2:21
ዕብ. 10:26ማቴ 12:32፤ ዕብ 6:4-6፤ 1ዮሐ 5:16
ዕብ. 10:27ኢሳ 26:11
ዕብ. 10:28ዘዳ 17:6
ዕብ. 10:29ማቴ 26:27, 28፤ ሉቃስ 22:20
ዕብ. 10:29ዕብ 6:4-6
ዕብ. 10:30ዘዳ 32:35, 36
ዕብ. 10:322ቆሮ 4:6፤ ዕብ 6:4
ዕብ. 10:34ሉቃስ 16:9
ዕብ. 10:34ማቴ 5:12
ዕብ. 10:35ማቴ 10:32፤ 1ቆሮ 15:58
ዕብ. 10:36ሉቃስ 21:19፤ ያዕ 5:11
ዕብ. 10:37ኢሳ 26:20
ዕብ. 10:37ዕን 2:3፤ 2ጴጥ 3:9
ዕብ. 10:38ዮሐ 3:16፤ ሮም 1:17
ዕብ. 10:38ዕን 2:4
ዕብ. 10:392ጴጥ 2:20
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
  • 32
  • 33
  • 34
  • 35
  • 36
  • 37
  • 38
  • 39
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዕብራውያን 10:1-39

ለዕብራውያን የተጻፈ ደብዳቤ

10 ሕጉ ወደፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ+ ነው እንጂ የእነዚህ ነገሮች እውነተኛ አካል አይደለም፤ ስለዚህ ሕጉ ከዓመት ዓመት እነዚያኑ መሥዋዕቶች በማቅረብ አምላክን የሚያመልኩትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም።*+ 2 ቢችልማ ኖሮ መሥዋዕት ማቅረቡን ይተዉት አልነበረም? ምክንያቱም ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ሰዎች አንዴ ከነጹ በኋላ ሕሊናቸው በጥፋተኝነት ስሜት አይወቅሳቸውም ነበር። 3 ይሁንና እነዚህ መሥዋዕቶች ከዓመት ዓመት ኃጢአት እንዲታወስ ያደርጋሉ፤+ 4 የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ አይችልምና።

5 ስለዚህ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “‘መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ ከዚህ ይልቅ አካል አዘጋጀህልኝ። 6 ሙሉ በሙሉ በሚቃጠል መባና ለኃጢአት በሚቀርብ መባ ደስ አልተሰኘህም።’+ 7 በዚህ ጊዜ ‘እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ (ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል እንደተጻፈ) ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ’ አልኩ።”+ 8 በመጀመሪያ እንዲህ አለ፦ “መሥዋዕትን፣ መባን፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባንና ለኃጢአት የሚቀርብ መባን አልፈለግክም፤ እንዲሁም ደስ አልተሰኘህበትም።” እነዚህ መሥዋዕቶች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የሚቀርቡ ናቸው። 9 ከዚያም “እነሆ፣ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ።+ ሁለተኛውን ለማቋቋም የመጀመሪያውን ያስወግዳል። 10 በዚህ “ፈቃድ”+ መሠረት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ በቀረበው የኢየሱስ ክርስቶስ አካል አማካኝነት ተቀድሰናል።+

11 በተጨማሪም እያንዳንዱ ካህን ቅዱስ አገልግሎት ለማቅረብና*+ ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የማይችሉትን+ እነዚያኑ መሥዋዕቶች በየጊዜው ለማቅረብ+ ዕለት ዕለት በቦታው ይገኛል። 12 ይህ ሰው ግን ስለ ኃጢአት ለሁልጊዜ የሚሆን አንድ መሥዋዕት አቅርቦ በአምላክ ቀኝ ተቀምጧል፤+ 13 ከዚያን ጊዜ አንስቶ ጠላቶቹ የእግሩ መርገጫ እስኪደረጉ ድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።+ 14 እነዚያን የሚቀደሱትን ለሁልጊዜ ፍጹማን ያደረጋቸው አንድ መሥዋዕት በማቅረብ ነውና።+ 15 ከዚህ በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስም ስለ እኛ ይመሠክራል፤ በመጀመሪያ እንዲህ ይላልና፦ 16 “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ።* ‘ሕግጋቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በአእምሯቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።’”+ 17 በመቀጠልም “ኃጢአታቸውንና የዓመፅ ድርጊታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም” ይላል።+ 18 እንግዲህ እነዚህ ይቅር ከተባሉ፣ ከዚህ በኋላ ለኃጢአት መባ ማቅረብ አያስፈልግም።

19 ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅዱሱ ስፍራ በሚወስደው መንገድ ለመግባት የሚያስችል ድፍረት* አግኝተናል፤+ 20 እሱ የከፈተልን* ይህ መንገድ ወደ ሕይወት የሚመራ አዲስ መንገድ ነው። ይህን ያደረገው በመጋረጃው+ ማለትም በሥጋው በኩል በማለፍ ነው፤ 21 በተጨማሪም በአምላክ ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን+ 22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት+ ልባችንን ተረጭተን እንዲሁም ሰውነታችንን በንጹሕ ውኃ ታጥበን+ በቅን ልቦና እና በሙሉ እምነት ወደ አምላክ እንቅረብ። 23 የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ስለሆነ ተስፋችንን በይፋ ለማወጅ የሚያስችለንን አጋጣሚ ያላንዳች ማወላወል አጥብቀን እንያዝ።+ 24 እንዲሁም እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት* እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤*+ 25 አንዳንዶች ልማድ እንዳደረጉት መሰብሰባችንን* ቸል አንበል፤+ ከዚህ ይልቅ እርስ በርስ እንበረታታ፤+ ደግሞም ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስናይ ከበፊቱ ይበልጥ ይህን እናድርግ።+

26 የእውነትን ትክክለኛ እውቀት ካገኘን በኋላ ሆን ብለን በኃጢአት ጎዳና ብንመላለስ+ ለኃጢአታችን የሚቀርብ ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤+ 27 ከዚህ ይልቅ አስፈሪ ፍርድ ይጠብቀናል፤ አምላክን የሚቃወሙትን የሚበላ የሚነድ ቁጣም ይኖራል።+ 28 የሙሴን ሕግ የጣሰ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሠከሩበት ያለርኅራኄ ይገደል ነበር።+ 29 ታዲያ የአምላክን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳኑን ደም+ እንደ ተራ ነገር የቆጠረና የጸጋን መንፈስ በንቀት ያጥላላ ሰው ምን ያህል የከፋ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?+ 30 “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና። ደግሞም “ይሖዋ* ሕዝቡን ይዳኛል።”+ 31 በሕያው አምላክ እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነገር ነው።

32 ይሁን እንጂ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ+ በመከራ ውስጥ በከፍተኛ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀድሞውን ጊዜ ዘወትር አስታውሱ። 33 በአደባባይ ለነቀፋና ለመከራ የተጋለጣችሁባቸው* ጊዜያት ነበሩ፤ ደግሞም እንዲህ ዓይነት ሁኔታ የደረሰባቸውን ሰዎች መከራ የተጋራችሁባቸው* ጊዜያት ነበሩ። 34 እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ዘላቂ የሆነ ንብረት እንዳላችሁ ስለምታውቁ+ በእስር ላይ ላሉት ራራችሁላቸው፤ እንዲሁም ንብረታችሁ ሲዘረፍ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ።+

35 እንግዲህ ትልቅ ወሮታ የሚያስገኘውን በድፍረት የመናገር ነፃነታችሁን አሽቀንጥራችሁ አትጣሉት።+ 36 የአምላክን ፈቃድ ከፈጸማችሁ በኋላ የተስፋው ቃል ሲፈጸም ማየት እንድትችሉ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።+ 37 ምክንያቱም “ለጥቂት ጊዜ ነው”+ እንጂ “የሚመጣው እሱ ይመጣል፤ ደግሞም አይዘገይም።”+ 38 “ሆኖም ጻድቅ አገልጋዬ በእምነት ይኖራል”፤+ ደግሞም “ወደኋላ ቢያፈገፍግ በእሱ ደስ አልሰኝም።”*+ 39 እንግዲህ እኛ በሕይወት የሚያኖር* እምነት እንዳላቸው ሰዎች ነን እንጂ ወደ ጥፋት እንደሚያፈገፍጉ ሰዎች አይደለንም።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ