ሚክያስ
3 እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችና
የእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ።+
ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም?
3 የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤+
ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤
አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤+
በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል* ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ።
4 በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤
እሱ ግን አይመልስላቸውም።
5 ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣+
በጥርሳቸው ሲነክሱ*+ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣+
አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ* ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
ፀሐይ በነቢያቱ ላይ ትጠልቅባቸዋለች፤
ቀኑም ወደ ጨለማ ይለወጥባቸዋል።+
7 ባለ ራእዮች ኀፍረት ይከናነባሉ፤+
ሟርተኞችም ይዋረዳሉ።
ከአምላክ ዘንድ መልስ ስለማይኖር
ሁሉም አፋቸውን* ይሸፍናሉ።’”
8 እኔ በበኩሌ ለያዕቆብ ዓመፁን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን እንድነግር
በይሖዋ መንፈስ ኃይልን፣
ፍትሕንና ብርታትን ተሞልቻለሁ።
9 ፍትሕን የምትጸየፉና ቀና የሆነውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፣+
እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣
የእስራኤልም ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ይህን ስሙ፤+
10 ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምንም በዓመፅ የምትገነቡ፣ ስሙ።+
ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም?+
ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም”+
እያሉ በይሖዋ ይመካሉ።*