ሆሴዕ የመጽሐፉ ይዘት 1 የሆሴዕ ሚስትና የወለደቻቸው ልጆች (1-9) ኢይዝራኤል (4)፣ ሎሩሃማ (6) እና ሎአሚ (9) አንድ እንደሚሆኑ የተነገረ ተስፋ (10, 11) 2 ከዳተኛዋ እስራኤል ተቀጣች (1-13) ወደ ይሖዋ ይመለሳሉ (14-23) “ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ” (16) 3 ሆሴዕ አመንዝራ የሆነችውን ሚስቱን መልሶ ወሰዳት (1-3) እስራኤላውያን ተመልሰው ወደ ይሖዋ ይመጣሉ (4, 5) 4 ይሖዋ ከእስራኤል ጋር ይፋረዳል (1-8) በምድሪቱ ላይ አምላክን ማወቅ የለም (1) የእስራኤል የጣዖት አምልኮና ሴሰኝነት (9-19) የአመንዝራነት መንፈስ እንዲባዝኑ ያደርጋል (12) 5 በኤፍሬምና በይሁዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-15) 6 ወደ ይሖዋ እንዲመለሱ የቀረበ ጥሪ (1-3) ሕዝቡ ታማኝ ፍቅር ማሳየቱን አልቀጠለም (4-6) ታማኝ ፍቅር ከመሥዋዕት ይበልጣል (6) የሕዝቡ ምግባር አሳፋሪ ነው (7-11) 7 የኤፍሬም ክፋት ተገለጸ (1-16) ከአምላክ መረብ ማምለጥ አይቻልም (12) 8 ጣዖት አምልኮ የሚያስከትለው መዘዝ (1-14) “ነፋስን ይዘራሉ፤ አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ” (7) “እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል” (14) 9 የኤፍሬም ኃጢአት በአምላክ ፊት ተቀባይነት አሳጣው (1-17) ለአሳፋሪው አምላክ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ (10) 10 የተበላሸ ወይን የሆነው እስራኤል ጥፋት ይደርስበታል (1-15) መዝራትና ማጨድ (12, 13) 11 “እስራኤል ገና ልጅ ሳለ ወደድኩት” (1-12) ‘ልጄን ከግብፅ ጠራሁት’ (1) 12 ኤፍሬም ወደ ይሖዋ መመለስ ይኖርበታል (1-14) ያዕቆብ ከአምላክ ጋር ታገለ (3) ያዕቆብ የአምላክን ሞገስ ለማግኘት አልቅሶ ለመነ (4) 13 ጣዖት አምላኪ የሆነው ኤፍሬም ይሖዋን ረሳ (1-16) “ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?” (14) 14 ወደ ይሖዋ ለመመለስ የቀረበ ልመና (1-3) የከንፈር ውዳሴ ማቅረብ (2) “ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ” (4-9)