ሆሴዕ
1 በይሁዳ ነገሥታት+ በዖዝያ፣+ በኢዮዓታም፣+ በአካዝና+ በሕዝቅያስ+ እንዲሁም በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ+ ልጅ በኢዮርብዓም+ ዘመን ወደ ቤኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ* የመጣው የይሖዋ ቃል። 2 ይሖዋ በሆሴዕ አማካኝነት ቃሉን መናገር ሲጀምር ይሖዋ ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሄደህ ዝሙት አዳሪ ሴት* አግባ፤ እሷ በምትፈጽመውም ምንዝር* ልጆች ይወለዱልሃል፤ ምክንያቱም በምንዝር የተነሳ* ምድሪቱ ይሖዋን ከመከተል ሙሉ በሙሉ ርቃለች።”+
3 ስለዚህ ሄዶ የዲብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት።
4 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ልጁን ኢይዝራኤል* ብለህ ጥራው፤ በኢይዝራኤል* ለፈሰሰው ደም የኢዩን ቤት በቅርቡ ተጠያቂ አደርጋለሁና፤+ የእስራኤል ቤት ንጉሣዊ አገዛዝም እንዲያከትም አደርጋለሁ።+ 5 በዚያ ቀን የእስራኤልን ቀስት በኢይዝራኤል ሸለቆ* እሰብራለሁ።”6 እሷም ዳግመኛ ፀነሰች፤ ሴት ልጅም ወለደች። አምላክም እንዲህ አለው፦ “ልጅቷን ሎሩሃማ* ብለህ ጥራት፤ ምክንያቱም ከእንግዲህ ለእስራኤል ቤት ምሕረት አላሳይም፤+ በእርግጥ አስወግዳቸዋለሁ።+ 7 ለይሁዳ ቤት ግን ምሕረት አደርጋለሁ፤+ በቀስት፣ በሰይፍ፣ በጦርነት፣ በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በይሖዋ አድናቸዋለሁ።”+
8 ጎሜር፣ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለች በኋላ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። 9 ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው፦ “ልጁን ሎአሚ* ብለህ ጥራው፤ ምክንያቱም እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም፤ እኔም አምላካችሁ አይደለሁም።
10 “የእስራኤልም ሕዝብ* ብዛት ሊሰፈር ወይም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል።+ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’+ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ይባላሉ።+ 11 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ተሰብስበው አንድ ይሆናሉ፤+ ለራሳቸውም አንድ መሪ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።+
እህቶቻችሁን ደግሞ ‘ምሕረት የተደረገልሽ ሴት!’* በሏቸው።+
2 እናታችሁን ክሰሷት፤ እሷ ሚስቴ ስላልሆነች፣+
እኔም ባሏ ስላልሆንኩ ክሰሷት።
ከእሷ ዘንድ ዘማዊነቷን፣*
ከጡቶቿም መካከል ምንዝሯን ታስወግድ፤
3 አለዚያ ራቁቷን አስቀራታለሁ፤ በተወለደችበት ቀን እንደነበረችውም አደርጋታለሁ፤
እንደ ምድረ በዳ፣
ውኃ እንደሌለበትም ምድር አደርጋታለሁ፤
በውኃ ጥምም እገድላታለሁ።
4 ወንዶች ልጆቿ የምንዝር* ልጆች ስለሆኑ
ምሕረት አላደርግላቸውም።
እነሱን የፀነሰችው ሴት አሳፋሪ ድርጊት ፈጽማለች፤+
‘አጥብቀው የሚወዱኝን፣
ደግሞም ምግቤንና ውኃዬን፣
የሱፍ ልብሴንና በፍታዬን እንዲሁም ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝን ተከትዬ እሄዳለሁ’ ብላለችና።+
6 ስለዚህ መንገዷን በእሾህ አጥር እዘጋለሁ፤
መውጫ መንገድ እንዳታገኝም
ዙሪያዋን በድንጋይ አጥራለሁ።
7 አጥብቀው የሚወዷትን ተከትላ ትሄዳለች፤ ሆኖም አትደርስባቸውም፤+
ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም።
8 እህሉን፣ አዲሱን የወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋት
እንዲሁም ለባአል አምልኮ የተጠቀሙበትን ብርና ወርቅ+
በብዛት እንድታገኝ ያደረግኩት እኔ እንደሆንኩ አልተገነዘበችም።+
10 አሁንም ኀፍረተ ሥጋዋን አጥብቀው በሚወዷት ፊት እገልጣለሁ፤
ከእጄም የሚያስጥላት ሰው አይኖርም።+
11 ደስታዋን፣ በዓሏን፣ የወር መባቻዋንና ሰንበቷን ሁሉ
እንዲሁም የተወሰኑትን የበዓል ወቅቶቿን ሁሉ አስቀራለሁ።+
12 “አጥብቀው የሚወዱኝ ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ደሞዜ ናቸው” የምትላቸውን
የወይን ተክሏንና የበለስ ዛፏን አወድማለሁ፤
ጫካም አደርጋቸዋለሁ፤
የዱር አራዊትም ይበሏቸዋል።
13 ለባአል ምስሎች መሥዋዕት ባቀረበችባቸው፣+ በጉትቻዋና በጌጦቿ በተንቆጠቆጠችባቸው
እንዲሁም አጥብቀው የሚወዷትን በተከተለችባቸው ቀናት የተነሳ ተጠያቂ አደርጋታለሁ፤
እኔንም ረስታኝ ነበር’+ ይላል ይሖዋ።
14 ‘ስለዚህ አግባብቼ አሳምናታለሁ፤
ወደ ምድረ በዳ እመራታለሁ፤
ልቧን በሚማርክ መንገድ አናግራታለሁ።
15 ከዚያን ጊዜ አንስቶ የወይን እርሻዎቿን መልሼ እሰጣታለሁ፤+
የአኮርም ሸለቆ*+ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤
በዚያም እንደ ልጅነቷ ጊዜና
ከግብፅ ምድር እንደወጣችበት ቀን መልስ ትሰጠኛለች።+
16 በዚያም ቀን’ ይላል ይሖዋ፣
‘ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ጌታዬ* ብለሽ አትጠሪኝም።’
18 በዚያም ቀን ለእነሱ ጥቅም ስል ከዱር አራዊት፣+
ከሰማይ ወፎችና መሬት ለመሬት ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤+
ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤+
20 በታማኝነት አጭሻለሁ፤
አንቺም በእርግጥ ይሖዋን ታውቂያለሽ።’+
21 ‘በዚያም ቀን መልስ እሰጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤
‘ለሰማያት መልስ እሰጣለሁ፤
እነሱ ደግሞ ለምድር መልስ ይሰጣሉ፤+
22 ምድር ደግሞ ለእህሉ፣ ለአዲሱ የወይን ጠጅና ለዘይቱ መልስ ትሰጣለች፤
እነሱ ደግሞ “አንተ አምላኬ ነህ” ይላሉ።’”+
3 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሌሎች አማልክትን የሚከተሉና+ የዘቢብ ቂጣ* የሚወዱ ሆነው ሳለ ይሖዋ እንደወደዳቸው ሁሉ፣+ አንተም ሄደህ በሌላ ሰው የተወደደችውንና ምንዝር የምትፈጽመውን ሴት ዳግመኛ ውደዳት።”+
2 በመሆኑም በ15 የብር ሰቅልና በአንድ ተኩል የሆሜር* መስፈሪያ ገብስ ለራሴ ገዛኋት። 3 ከዚያም እንዲህ አልኳት፦ “ለብዙ ቀናት የእኔ ሆነሽ ትቀመጫለሽ። አታመንዝሪ፤* ከሌላ ሰውም ጋር ግንኙነት አታድርጊ፤ እኔም ከአንቺ ጋር ግንኙነት አልፈጽምም።”4 ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ያለንጉሥ፣+ ያለገዢ፣ ያለመሥዋዕት፣ ያለዓምድ፣ ያለኤፉድና+ ያለተራፊም ምስል*+ ይኖራሉ። 5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ተመልሰው አምላካቸውን ይሖዋንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤+ በዘመኑም መጨረሻ ወደ ይሖዋና ወደ ጥሩነቱ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+
4 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣
ይሖዋ ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ስለሚፋረድ የይሖዋን ቃል ስሙ፤+
ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ እውነት፣ ታማኝ ፍቅርና አምላክን ማወቅ የለም።+
5 ስለዚህ እናንተ በጠራራ ፀሐይ ትሰናከላላችሁ፤
የጨለመ ይመስል ነቢዩም ከእናንተ ጋር ይሰናከላል።
እናታችሁንም ጸጥ አሰኛታለሁ።*
6 ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ይጠፋል።
7 እነሱ በበዙ ቁጥር በእኔ ላይ የሚሠሩት ኃጢአት በዝቷል።+
ክብራቸውን ወደ ውርደት እለውጣለሁ።*
8 የሕዝቤ ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፤
ደግሞም እነሱ በደል እንዲሠሩ ይቋምጣሉ።*
10 ይበላሉ፤ ሆኖም አይጠግቡም።+
12 ሕዝቤ ከእንጨት የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን ያማክራሉ፤
በትራቸው* የሚላቸውን ነገር ያደርጋሉ፤
ምክንያቱም የአመንዝራነት* መንፈስ እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል፤
በአመንዝራነታቸው* የተነሳም ለአምላካቸው ለመገዛት አሻፈረን ይላሉ።
13 በተራሮች አናት ላይ ይሠዋሉ፤+
ደግሞም በኮረብቶች ላይ
እንዲሁም በባሉጥ ዛፎች፣ በሊብነህ ዛፎችና* በትልቅ ዛፍ ሁሉ ሥር የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ፤+
ምክንያቱም የዛፎቹ ጥላ መልካም ነው።
ከዚህም የተነሳ ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች* ይሆናሉ፤
ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ።
14 ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች* በመሆናቸው፣
ምራቶቻችሁም በማመንዘራቸው አልቀጣቸውም።
16 እስራኤል እንደ እልኸኛ በሬ እልኸኛ ሆናለችና።+
ታዲያ ይሖዋ እንደ በግ ጠቦት በተንጣለለ የግጦሽ መስክ* ያሰማራቸዋል?
17 ኤፍሬም ከጣዖቶች ጋር ተቆራኝቷል።+
በቃ ተዉት!
19 ነፋስ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፤*
እነሱም ባቀረቧቸው መሥዋዕቶች ያፍራሉ።”
5 “እናንተ ካህናት፣ ይህን ስሙ፤+
እናንተ የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ በትኩረት አዳምጡ፤
እናንተም የንጉሡ ቤት ሰዎች፣ አዳምጡ፤
ፍርዱ እናንተንም ይጨምራልና፤
ምክንያቱም ለምጽጳ ወጥመድ፣
በታቦርም+ ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
3 ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤
እስራኤልም ከእኔ የተሰወረ አይደለም።
6 መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ይዘው ይሖዋን ፍለጋ ሄዱ፤
ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም።
እሱ ከእነሱ ርቋል።+
7 እነሱ ይሖዋን ከድተዋል፤+
ባዕድ ወንዶች ልጆች ወልደዋልና።
አሁንም አንድ ወር፣ እነሱንና ድርሻቸውን* ይውጣል።*
8 በጊብዓ ቀንደ መለከት፣ በራማም+ መለከት ንፉ!+
‘ቢንያም ሆይ፣ ከኋላህ ነን!’ ብላችሁ በቤትአዌን+ ቀረርቶ አሰሙ።
9 ኤፍሬም ሆይ፣ በምትቀጣበት ቀን መቀጣጫ ትሆናለህ።+
በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ምን እንደሚከሰት አሳውቄአለሁ።
10 የይሁዳ መኳንንት ወሰን እንደሚገፉ ሰዎች ናቸው።+
በእነሱ ላይ ቁጣዬን እንደ ውኃ አፈሳለሁ።
11 ኤፍሬም ተጨቁኗል፤ በፍርድ ተረግጧል፤
ባላጋራውን ለመከተል ቆርጧልና።+
12 በመሆኑም እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣
ለይሁዳ ቤት ደግሞ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ።
13 ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቁስሉን ሲመለከት
ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤+ ወደ ታላቅ ንጉሥም መልእክተኞች ላከ።
ይሁንና ንጉሡ እናንተን ሊፈውሳችሁ አልቻለም፤
ቁስላችሁንም ሊያድን አልቻለም።
14 እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣
ለይሁዳም ቤት እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና።
በጭንቀት በሚዋጡበት ጊዜ እኔን ይሻሉ።”+
6 “ኑ ወደ ይሖዋ እንመለስ፤
እሱ ቦጫጭቆናል፤+ ሆኖም ይፈውሰናል።
እሱ መቶናል፤ ሆኖም ቁስላችንን ይጠግናል።
2 ከሁለት ቀናት በኋላ ያነቃናል።
በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል፤
እኛም በፊቱ እንኖራለን።
3 ይሖዋን እናውቀዋለን፤ እሱን ለማወቅ ልባዊ ጥረት እናደርጋለን።
የእሱ መውጣት እንደ ንጋት ብርሃን የተረጋገጠ ነው፤
እንደ ዶፍ ዝናብ፣ ምድርንም እንደሚያጠግበው የኋለኛው ዝናብ
ወደ እኛ ይመጣል።”
4 “ኤፍሬም ሆይ፣ ምን ላድርግህ?
ይሁዳ ሆይ፣ ምን ላድርግህ?
ታማኝ ፍቅራችሁ እንደ ጠዋት ጉም፣
ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ነውና።
በእናንተም ላይ የምፈርደው ፍርድ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል።+
7 እነሱ ግን እንደ ተራ ሰዎች ቃል ኪዳኑን ተላለፉ።+
በዚያም እኔን ከዱኝ።
9 የካህናቱ ማኅበር ሰውን አድብቶ እንደሚጠብቅ የወራሪዎች ቡድን ነው።
በሴኬም+ መንገድ ላይ ሰው ይገድላሉ፤
ምግባራቸው አሳፋሪ ነውና።
10 በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ።
11 በአንጻሩ ግን ይሁዳ ሆይ፣ የሕዝቤን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜ
መከር ይጠብቅሃል።”+
2 እነሱ ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ ልብ አይሉም።+
የገዛ ድርጊታቸው ከቧቸዋል፤
የሠሩት ሥራ ሁሉ በፊቴ ነው።
3 ንጉሡን በክፋታቸው፣
መኳንንቱንም አታላይ በሆነ ድርጊታቸው ያስደስታሉ።
4 ሁሉም አመንዝሮች ናቸው፤
አንድ ዳቦ ጋጋሪ እሳቱን አንዴ ካቀጣጠለው በኋላ፣
ያቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንደማያስፈልገው የጋለ ምድጃ ናቸው።
5 በንጉሣችን ክብረ በዓል ቀን፣ መኳንንቱ ታመሙ፤
በወይን ጠጅ የተነሳ በቁጣ ተሞሉ።+
ንጉሡ ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ።
6 እንደ ምድጃ የሚነድ ልብ ይዘው ይቀርባሉና።*
ዳቦ ጋጋሪው ሌሊቱን ሙሉ ይተኛል፤
በማለዳ ምድጃው እንደሚንበለበል እሳት ይንቀለቀላል።
7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤
ገዢዎቻቸውንም* ይውጣሉ።
8 ኤፍሬም ከብሔራት ጋር ይቀላቀላል።+
እሱ እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው።
9 እንግዶች ጉልበቱን በዘበዙ፤+ እሱ ግን ይህን አላወቀም።
ራሱንም ሽበት ወረሰው፤ እሱ ግን ይህን ልብ አላለም።
11 ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላት* ሞኝ ርግብ ነው።+
12 የትም ቢሄዱ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ።
እንደ ሰማይ ወፎች ወደ ታች አወርዳቸዋለሁ።
ለጉባኤያቸው በሰጠሁት ማስጠንቀቂያ መሠረት እገሥጻቸዋለሁ።+
13 ከእኔ ስለሸሹ ወዮላቸው!
በእኔ ላይ በደል ስለፈጸሙ ጥፋት ይምጣባቸው!
እነሱን ለመዋጀት ዝግጁ ነበርኩ፤ እነሱ ግን በእኔ ላይ ውሸት ተናገሩ።+
14 በአልጋቸው ላይ ሆነው ዋይ ዋይ ቢሉም
እርዳታ ለማግኘት ከልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም።+
ለእህላቸውና ለአዲስ የወይን ጠጃቸው ሲሉ ሰውነታቸውን ይተለትላሉ፤
በእኔም ላይ ዓመፁ።
15 ያሠለጠንኳቸውና ክንዳቸውን ያበረታሁ ቢሆንም
ክፉ ነገር በማሴር በእኔ ላይ ተነስተዋል።
አለቆቻቸው እብሪተኛ ከሆነው አንደበታቸው የተነሳ በሰይፍ ይወድቃሉ።
በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር መሳለቂያ ይሆናሉ።”+
8 “ቀንደ መለከት ንፋ!+
2 ‘አምላካችን ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች እናውቅሃለን!’ እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ።+
3 እስራኤል መልካም የሆነውን ነገር ገሸሽ አድርጓል።+
ጠላት ያሳደው።
4 እኔ ሳልላቸው ነገሥታትን አነገሡ።
መኳንንትን ሾሙ፤ እኔ ግን እውቅና አልሰጠኋቸውም።
5 ሰማርያ ሆይ፣ የጥጃ ጣዖትሽ ተጥሏል።+
ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል።+
ንጹሕ መሆን* የሚሳናቸው እስከ መቼ ነው?
6 ይህ ከእስራኤል ነውና።
የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም፤
የሰማርያ ጥጃ ተሰባብሮ እንዳልነበረ ይሆናል።
7 ነፋስን ይዘራሉ፤
አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ።+
8 የእስራኤል ሰዎች ይዋጣሉ።+
በብሔራት መካከል
ማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ይሆናሉ።+
9 ተገልሎ እንደሚኖር የዱር አህያ ወደ አሦር ሄደዋልና።+
ኤፍሬም በገንዘብ ፍቅረኞች አፍርቷል።+
11 ኤፍሬም ኃጢአት ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቷል።+
ኃጢአት የሚፈጽምባቸው መሠዊያዎች ሆነውለታል።+
13 መሥዋዕቶችን ስጦታ አድርገው ለእኔ ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤
ይሖዋ ግን በእነሱ አልተደሰተም።+
በደላቸውን ያስታውሳል፤ ለሠሯቸውም ኃጢአቶች ይቀጣቸዋል።+
እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤
እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።”+
9 “እስራኤል ሆይ፣ ሐሴት አታድርግ፤+
እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች ደስ አይበልህ።
በየእህል አውድማ ላይ ለዝሙት አዳሪ የሚከፈለውን ደሞዝ ወደኸዋል።+
2 ሆኖም የእህል አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፤
አዲሱም የወይን ጠጅ ይቋረጥባቸዋል።+
እንደ እዝን እንጀራ ናቸው፤
የሚበሉትም ሁሉ ራሳቸውን ያረክሳሉ።
ምግባቸው ለራሳቸው ብቻ* ነውና፤
ወደ ይሖዋ ቤት አይገባም።
5 የምትሰበሰቡበትና* ለይሖዋ በዓል የምታከብሩበት ቀን ሲደርስ
ምን ታደርጉ ይሆን?
6 እነሆ፣ ምድሪቱ በመውደሟ ለመሸሽ ይገደዳሉ።+
ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤+ ሜምፊስ ደግሞ ትቀብራቸዋለች።+
ከብር የተሠሩ ውድ ንብረቶቻቸውን ሳማ ይወርሰዋል፤
በድንኳኖቻቸውም ውስጥ እሾሃማ ቁጥቋጦ ይበቅላል።
የእነሱ ነቢይ ሞኝ፣ በመንፈስ የሚናገረውም ሰው እንደ እብድ ይሆናል፤
ምክንያቱም በደልህ ብዙ ነው፤ በአንተም ላይ የሚደርሰው ጥላቻ በዝቷል።”
አሁን ግን የነቢያቱ+ መንገዶች ሁሉ እንደ ወፍ አዳኝ ወጥመዶች ናቸው፤
በአምላኩ ቤት ጠላትነት አለ።
9 በጊብዓ ዘመን እንደነበረው፣ ጥፋት በሚያስከትሉ ነገሮች ተዘፍቀዋል።+
እሱ በደላቸውን ያስባል፤ በሠሩትም ኃጢአት የተነሳ ይቀጣቸዋል።+
10 “እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት።+
አባቶቻችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ባፈራ የበለስ ዛፍ ላይ እንደ ጎመራ የበለስ ፍሬ ሆነው አየኋቸው።
11 የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤
መውለድ፣ ማርገዝም ሆነ መፀነስ የለም።+
13 በግጦሽ ስፍራ የተተከለው ኤፍሬም ለእኔ እንደ ጢሮስ ነበር፤+
አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለእርድ አሳልፎ ይሰጣል።”
14 ይሖዋ ሆይ፣ ልትሰጣቸው የሚገባውን ስጣቸው፤
የሚጨነግፍ ማህፀንና የደረቁ* ጡቶች ስጣቸው።
15 “ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ በጊልጋል ፈጸሙ፤+ እኔም በዚያ ጠላኋቸው።
በሠሩት ክፉ ድርጊት የተነሳ ከቤቴ አባርራቸዋለሁ።+
ከእንግዲህ ወዲያ ፍቅሬን እነፍጋቸዋለሁ፤+
አለቆቻቸው ሁሉ እልኸኞች ናቸው።
16 ኤፍሬም ጉዳት ይደርስበታል።+
ሥራቸው ይደርቃል፤ አንዳችም ፍሬ አያፈሩም።
ቢወልዱ እንኳ የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”
10 “እስራኤል ፍሬ የሚሰጥ እየተበላሸ* ያለ ወይን ነው።+
2 ልባቸው ግብዝ* ነው፤
በመሆኑም በደለኞች ናቸው።
መሠዊያዎቻቸውን የሚሰባብር፣ ዓምዶቻቸውንም የሚያፈራርስ አለ።
3 እነሱም ‘ንጉሥ የለንም፤+ ይሖዋን አልፈራንምና።
ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ሊያደርግልን ይችላል?’ ይላሉ።
5 የሰማርያ ነዋሪዎች በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ስጋት ያድርባቸዋል።+
ሕዝቡም ሆኑ በእሱና በክብሩ ሐሴት ያደረጉት የባዕድ አምላክ ካህናት
ለእሱ ያዝናሉ፤
ከእነሱ ተለይቶ በግዞት ይወሰዳልና።
6 ለአንድ ታላቅ ንጉሥ እንደሚቀርብ ስጦታ ወደ አሦር ይወሰዳል።+
ኤፍሬም ውርደት ይከናነባል፤
እስራኤልም በተከተለው ምክር የተነሳ ያፍራል።+
7 ሰማርያና ንጉሧ ተቆርጦ ውኃ ላይ እንደወደቀ ቅርንጫፍ
ተጠራርገው ይጠፋሉ።+
8 የእስራኤል ኃጢአት+ የሆኑት በቤትአዌን+ የሚገኙ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ይወድማሉ።+
መሠዊያዎቻቸውን እሾህና አሜኬላ ይወርሷቸዋል።+
ሰዎች ተራሮቹን ‘ሸሽጉን!’
ኮረብቶቹንም ‘በላያችን ውደቁ!’ ይሏቸዋል።+
9 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኃጢአት ሠርታችኋል።+
እነሱ በዚያ ጸንተዋል።
በጊብዓ የተካሄደው ጦርነት የዓመፅን ልጆች አልፈጃቸውም።*
10 በፈለግኩ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ።
ሁለቱ በደሎቻቸው በላያቸው በሚጫኑበት ጊዜ*
ሕዝቦች በእነሱ ላይ ይሰበሰባሉ።
11 ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነው፤
በመሆኑም ያማረ አንገቷን አተረፍኩ።
ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ለእሱ ያለሰልሳል።
12 ለራሳችሁ የጽድቅን ዘር ዝሩ፤ ታማኝ ፍቅርንም እጨዱ።
14 በሕዝባችሁ ላይ ሁከት ይነሳል፤
እናቶች ከልጆቻቸው ጋር በተጨፈጨፉበት* የውጊያ ቀን
ሻልማን፣ ቤትአርቤልን እንዳወደመ ሁሉ፣
የተመሸጉ ከተሞቻችሁ በሙሉ ይወድማሉ።+
15 ቤቴል ሆይ፣ ክፋትሽ ታላቅ ስለሆነ እንዲሁ ይደረግብሻል።+
ጎህ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።”*+
4 በሰዎች ገመድ፣* በፍቅርም ማሰሪያ ሳብኳቸው፤+
ደግሞም ከጫንቃቸው ላይ* ቀንበር እንደሚያነሳ ሰው ሆንኩላቸው፤
ለእያንዳንዳቸውም በደግነት ምግብ አቀረብኩላቸው።
7 ሕዝቤ በእኔ ላይ ክህደት ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም።+
ወደ ላይ* ቢጠሯቸውም ማንም አይነሳም።
8 ኤፍሬም ሆይ፣ እንዴት ልተውህ እችላለሁ?+
እስራኤል ሆይ፣ እንዴት አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ?
እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ?
ደግሞስ እንዴት እንደ ጸቦይም ላደርግህ እችላለሁ?+
9 የሚነድ ቁጣዬን አልገልጽም።
12 “ኤፍሬም በውሸት፣
የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ።+
12 “ኤፍሬም ነፋስን ይመገባል።
ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል።
ውሸትንና ዓመፅን ያበዛል።
ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ፤+ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ።+
4 ከመልአክ ጋር መታገሉን ቀጠለ፤ ደግሞም አሸነፈ።
ሞገስ እንዲያሳየው አልቅሶ ለመነው።”+
7 ይሁንና በነጋዴው እጅ አታላይ ሚዛን አለ፤
እሱ ማጭበርበር ይወዳል።+
ደግሞም ከደከምኩበት ነገር ሁሉ ጋር በተያያዘ በደልም ሆነ ኃጢአት አያገኙብኝም’ ይላል።
9 ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ።+
በተወሰነው ጊዜ* እንደነበረው ሁሉ፣
እንደገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ።
13 “ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤
በእስራኤል ነገዶች መካከል ትልቅ ቦታ ነበረው።+
ሆኖም ባአልን በማምለክ በደል በመፈጸሙ+ ሞተ።
‘መሥዋዕት የሚያቀርቡት ሰዎች ጥጃዎቹን ይሳሙ’+ በማለት ለእነሱ ይናገራሉ።
3 ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣
ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ይሆናሉ፤
አውሎ ነፋስ ከአውድማ ላይ ጠራርጎ እንደሚወስደው እብቅ፣
በጭስ ማውጫም በኩል እንደሚወጣ ጭስ ይሆናሉ።
5 እኔ በምድረ በዳ፣ ድርቅ ባለበትም ምድር ተንከባከብኩህ።+
6 በግጦሽ መሬታቸው ላይ ከበሉ በኋላ ጠገቡ፤+
በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ።
ከዚህም የተነሳ ረሱኝ።+
7 ስለዚህ እንደ አንበሳ፣+
በመንገድም ዳር እንደሚያደባ ነብር እሆንባቸዋለሁ።
8 ግልገሎቿን እንደተነጠቀች ድብ ሆኜ እመጣባቸዋለሁ፤
ደረታቸውንም እዘነጥላለሁ።
በዚያ እንደ አንበሳ እውጣቸዋለሁ፤
የዱር አውሬ ይቦጫጭቃቸዋል።
9 እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ላይ ስለተነሳህ፣
ረዳትህንም ስለተቃወምክ ያጠፋሃል።
12 የኤፍሬም በደል ታሽጎ ተቀምጧል፤*
ኃጢአቱም ተከማችቷል።
13 ምጥ እንደያዛት ሴት ይሆናል።
እሱ ግን ጥበበኛ ልጅ አይደለም፤
የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ በቦታው ላይ አይገኝም።
ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ?+
መቃብር ሆይ፣ አጥፊነትህ የት አለ?+
ርኅራኄ ከዓይኔ ፊት ይሰወራል።
15 በቄጠማዎች መካከል ተመችቶት ቢያድግ እንኳ
የምሥራቅ ነፋስ ይኸውም የይሖዋ ነፋስ ይመጣል፤
የውኃ ጉድጓዱ እንዲደርቅ፣ ምንጩም እንዲነጥፍ ለማድረግ ከበረሃ ይመጣል።
ውድ የሆኑ ንብረቶቹ ሁሉ የሚገኙበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል።+
16 ሰማርያ በአምላኳ ላይ ስላመፀች+ ተጠያቂ ትሆናለች።+
14 “እስራኤል ሆይ፣ በበደልህ ስለተሰናከልክ
ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ተመለስ።+
2 ይህን ቃል ይዛችሁ ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤
እንዲህ በሉት፦ ‘በደላችንን ይቅር በለን፤+ መልካም የሆነውንም ነገር ተቀበለን፤
3 አሦር አያድነንም።+
4 እኔም ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ።+
5 እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤
እሱም እንደ አበባ ያብባል፤
እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥሮቹን ይሰዳል።
6 ቀንበጦቹ ይንሰራፋሉ፤
ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣
መዓዛውም እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይሆናል።
7 እነሱም ዳግመኛ በጥላው ሥር ይኖራሉ።
እህል ያበቅላሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ።+
ዝናው* እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይሆናል።
8 ኤፍሬም ‘ከእንግዲህ ከጣዖቶች ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?’ ይላል።+
መልስ እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም እጠብቀዋለሁ።+
እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ እሆናለሁ።
ከእኔም ፍሬ ታገኛላችሁ።”
9 ጥበበኛ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ያስተውል።
ልባም የሆነ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ይወቅ።
ሆሻያህ የሚለው ስም አጭር መጠሪያ ሲሆን “ያህ አዳነው፤ ያህ አድኗል” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “ነውረኛ ሴት፤ ሴሰኛ ሴት።”
ወይም “ነውር፤ ሴሰኝነት።”
ወይም “በነውር የተነሳ፤ በሴሰኝነት የተነሳ።”
“አምላክ ዘር ይዘራል” የሚል ትርጉም አለው።
ዋና ከተማዋ ሰማርያ ብትሆንም ኢይዝራኤል የሰሜናዊ እስራኤል ነገሥታት መቀመጫ ነበረች። 1ነገ 21:1ን ተመልከት።
ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
“ምሕረት አልተደረገላትም” የሚል ትርጉም አለው።
“ሕዝቤ አይደሉም” የሚል ትርጉም አለው።
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ሆሴዕ 1:9 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ሆሴዕ 1:6 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ወይም “ነውረኝነቷን፤ ሴሰኝነቷን።”
ወይም “የነውር፤ የሴሰኝነት።”
ወይም “ነውር ፈጽማለችና (ሴስናለችና)።”
ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
ወይም “የእኔ ባአል።”
ወይም “እንዲኖሩም።”
“አምላክ ዘር ይዘራል” የሚል ትርጉም አለው።
ሆሴዕ 1:6 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ሆሴዕ 1:9 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ለሐሰት አምልኮ የሚጠቀሙበትን ቂጣ ያመለክታል።
አንድ ሆሜር 220 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ነውር አትፈጽሚ (አትሴስኚ)።”
ወይም “የቤት ውስጥ አማልክት፤ ጣዖታት።”
ወይም “እናታችሁንም አጠፋታለሁ።”
ወይም “መመሪያ፤ ትምህርት።”
“ክብሬን በውርደት ለውጠዋል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሳቸው ትመኛለች።” የቃላት መፍቻው ላይ “ነፍስ” የሚለውን ተመልከት።
ወይም “እጅግ ነውረኛ ይሆናሉ፤ ያመነዝራሉ።”
ወይም “ነውረኝነት፤ ሴሰኝነት።”
ቃል በቃል “ልብ ያጠፋሉ።”
ወይም “የሟርተኛ ዘንጋቸው።”
ወይም “የነውረኝነት፤ የሴሰኝነት።”
ወይም “በነውረኝነታቸው፤ በሴሰኝነታቸው።”
ጥሩ መዓዛ ያላቸው ነጫጭ አበቦች የሚያወጣ ዛፍ።
ወይም “ነውረኞች፤ ሴሰኞች።”
ወይም “ነውረኞች፤ ሴሰኞች።”
ወይም “ነውር ብትፈጽሚም፤ ብትሴስኚም።”
ቃል በቃል “ሰፊ በሆነ ስፍራ።”
ወይም “ከስንዴ የሚዘጋጅ መጠጣቸው።”
ወይም “እጅግ ነውረኛ ይሆናሉ፤ ያመነዝራሉ።”
ቃል በቃል “ጋሻዎቿም።”
ወይም “ጠራርጎ ይወስዳታል።”
ወይም “ዓመፀኞቹ።”
ወይም “እጅግ ተጠላልፈዋል።”
ወይም “ሁሉንም እገሥጻለሁ።”
ወይም “እጅግ ነውረኛ ሆነሃል፤ አመንዝረሃል።”
ወይም “የነውረኝነት፤ የሴሰኝነት።”
ቃል በቃል “በፊቱ።”
ወይም “መሬታቸውን።”
“በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እነሱም ሆኑ ድርሻቸው ይዋጣሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ፊቴን።”
ወይም “ምሕረት።”
“ሴራ ጠንስሰው ሲቀርቡ ልባቸው እንደ ምድጃ ነውና” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ፈራጆቻቸውንም።”
ቃል በቃል “ልብ እንደሌላት።”
ላቅ ያለ አምልኮ መከተል አለመጀመራቸውን ያሳያል።
ወይም “ራሳቸውን ማንጻት።”
ወይም “ዛላ።”
ወይም “እንግዶች።”
ወይም “በመመሪያዬ፤ በትምህርቴ።”
“ይመለሳሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነውር በመፈጸም፤ ሴሰኛ በመሆን።”
ወይም “ለገዛ ነፍሳቸው።”
ወይም “የተወሰነው ክብረ በዓላችሁና።”
ወይም “ለአሳፋሪውም አምላክ።”
ወይም “የሟሸሹ።”
“እየተንሰራፋ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የማይታመን፤ መሠሪ።”
ወይም “ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።”
ቅጣታቸውን እንደ ቀንበር ሲሸከሙ ማለት ነው።
ወይም “በኤፍሬም ላይ ልጓም አስገባለሁ።”
ቃል በቃል “በተፈጠፈጡበት።”
ቃል በቃል “ጸጥ ይደረጋል።”
እስራኤልን ለማስተማር የተላኩትን ነቢያትና ሌሎች ሰዎች ያመለክታል።
ወይም “በደግነት ገመድ።” አንድ ወላጅ የሚጠቀምበትን ገመድ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ከመንጋጋቸው።”
ላቅ ያለ አምልኮን ያመለክታል።
ቃል በቃል “ግሏል።”
ወይም “ከአምላክ ጋር ይዞራል።”
ወይም “የሚታወስበት ስም።”
“በበዓል ጊዜ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ምትሃትና፤ አስማትና።”
ወይም “ሶርያ።”
ወይም “ቀልጠው የተሠሩ ሐውልቶች።”
ቃል በቃል “ፈራጆችህስ።”
ወይም “ተጠብቋል።”
ወይም “ከሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “እኛም በምላሹ የከንፈሮቻችንን ወይፈኖች እናቀርባለን።”
ቃል በቃል “መታሰቢያው።”