መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት።
3 ንዴትህን ሁሉ ገታህ፤
ከብርቱ ቁጣህም ተመለስክ።+
5 በእኛ ላይ የምትቆጣው ለዘላለም ነው?+
ቁጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይዘልቃል?
6 ሕዝቦችህ በአንተ ሐሴት እንዲያደርጉ፣
ዳግመኛ እንድናንሰራራ አታደርገንም?+
7 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህን አሳየን፤+
ማዳንህንም ለግሰን።
8 እውነተኛው አምላክ ይሖዋ የሚናገረውን እሰማለሁ፤
እሱ ለሕዝቡና ለታማኝ አገልጋዮቹ ስለ ሰላም ይናገራልና፤+
ብቻ እንደቀድሞው በራሳቸው ከልክ በላይ አይተማመኑ።+
9 ክብሩ በምድራችን እንዲኖር፣
እሱን ለሚፈሩት ማዳኑ በእርግጥ ቅርብ ነው።+
10 ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ይገናኛሉ፤
ጽድቅና ሰላም ይሳሳማሉ።+
11 ታማኝነት ከምድር ትበቅላለች፤
ጽድቅም ከሰማያት ወደ ታች ይመለከታል።+
13 ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤+
ለእርምጃውም መንገድ ያዘጋጃል።