የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 1/8 ገጽ 30-31
  • ከዓለም አካባቢ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከዓለም አካባቢ
  • ንቁ!—1999
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የውኃ ችግር
  • የቢሮ የቡና ስኒዎች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ
  • ልጆች ቀላል መዝናኛዎችን ይመርጣሉ
  • በቡልጋሪያ የተደረገ የደም ሴሚናር
  • የስፔይን ልጆችና ቴሌቪዥን
  • የቻይና ታሪክ የበለጠ ዕድሜ እንዳለው ታወቀ
  • ሙዚቃ በሸማቾች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል
  • ላሞችም ይመቻቸው
  • በጥላ ውስጥም ቆዳ ሊቃጠል ይችላል
  • ብክለት በመኪና አሽከርካሪዎች ላይ የሚያሳድረው አደጋ
  • በቡልጋሪያ የተደረገው ልዩ ዘመቻ ውጤት አስገኘ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2002
  • የኤክስፐርመንታል ፊዚክስ ሊቅ ስለሚያምንበት ነገር ምን ይላል?
    ንቁ!—2014
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—1994
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1999
g99 1/8 ገጽ 30-31

ከዓለም አካባቢ

የውኃ ችግር

ሌክስፕሬስ የተባለው ፈረንሳይኛ መጽሔት “አንድ ነገር ካልተደረገ በስተቀር ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው የሰው ዘር ከ2025 ዓመት በፊት በውኃ ጥም ይሠቃያል” በማለት ገልጿል። ለ ፊጋሮ የተባለው ጋዜጣ “በአሁኑ ጊዜ አንድ አራተኛው የዓለም ሕዝብ የመጠጥ ውኃ በቀጥታ አያገኝም” ይላል። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት ለውኃ ችግር መፍትሔ ለማፈላለግ በመጋቢት ወር 1998 በፓሪስ ከተማ አንድ ጉባኤ አዘጋጅቶ ነበር። የፈረንሳይን ፕሬዚዳንት ጨምሮ ከ84 አገሮች የተውጣጡት 200 ልዑካን ለዓለም የውኃ ምንጮች ተገቢውን ጥበቃ ስለማድረግ ተወያይተዋል። ትኩረት ከተሰጣቸው ችግሮች መካከል አንዱ አባካኝ በሆኑ የመስኖ ዘዴዎችና በተቀደዱ የውኃ ቧንቧዎች ምክንያት ብዙ ውኃ አላግባብ የሚባክን መሆኑ ነው። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ ውኃ የመላው የሰው ዘር የጋራ ቅርስ በመሆኑ ዓለም አቀፋዊ የሆነ ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ አጥብቀው ተናግረዋል።

የቢሮ የቡና ስኒዎች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ

“የቢሮ ሠራተኞች ስኒዎቻቸውን በጥንቃቄ ስለማያጥቡ ወይም ዕቃ የሚያጥቡበትን ቦታና ምግብ የሚያዘጋጁባቸውን አካባቢዎች በመርዝ ስለማያጸዷቸው እንደ ኢ ኮሊ ያሉት አደገኛ ባክቴሪያዎችን ጨምሮ ጥቃቅን ተውሳኮች በጣም በመባዛት ላይ ናቸው” ሲል ዘ ቶሮንቶ ስታር ዘግቧል። ቻርልስ ገርብ እና ራልፍ ሚር የተባሉት ተመራማሪዎች 12 ቢሮዎች የሚገኙ ስኒዎችንና የቡና ማፍያ ጀበናዎችን መርምረዋል። 40 በመቶ የሚሆኑት ስኒዎችና 20 በመቶ የሚሆኑት ዕቃ ማጠቢያ አካባቢ የሚቀመጡ ስፖንጆች ኮሊን የመሰሉ ባክቴሪያዎች፣ አንዳንዴም አደገኛ የሆነው ኢ ኮሊ ባክቴሪያ ተገኝቶባቸዋል። “ይህ የሚያመለክተው ጥሩ የንጽሕና አጠባበቅ አለመኖሩን ነው” ይላሉ ገርብ። ሪፖርቱ በማጠቃለያው ላይ “የዕቃ ማጠቢያ ማሽን ካልኖረ የቡና ስኒዎች በትኩስ ውኃና በሳሙና ከታጠቡ በኋላ ጀርሞችን የሚገድል መርዝ በተጨመረበት ውኃ ውስጥ ተዘፍዝፈው መቆየት አለባቸው። መወልወያ ጨርቆችና ስፖንጆች ቶሎ ቶሎ መጽዳት አለባቸው” ብሏል።

ልጆች ቀላል መዝናኛዎችን ይመርጣሉ

በልጆቻችሁ ዘንድ ጥሩ እናቶች መሆን የምትችሉት እንዴት ነው? ወርልፑል ፋውንደሽን የተባለው ድርጅት ከ6 እስከ 17 ዓመት ዕድሜ ባላቸው 1,000 አሜሪካውያን ልጆች ላይ ባደረገው ጥናት ብዙ ልጆች ዕለታዊ የሆኑ የተለመዱ ነገሮች ከእናቶቻቸው ጋር መሥራትን እንደሚመርጡ አረጋግጧል። የሚፈልጉት “አብሮ መሆንን” ብቻ ነው። ልጆች ከሁሉ በላይ የሚወዱት ከእናታቸው ጋር “አብሮ መብላትን ነው።” ሁለተኛ ምርጫቸው “አብሮ ለመብላት ወደ ውጭ ወጣ ማለት” እና “ገበያ አብሮ መገብየት” ናቸው። ከእነዚህ ከሁለቱ በሦስተኛ ደረጃ የሚከተለው “ቁጭ ብሎ አብሮ ማውራት” ነው። ልጆች እናቶቻቸውን ለማመስገን የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎችም በተመሳሳይ ቀላሎች ናቸው። ሰባ በመቶ የሚሆኑት አብዛኛውን ጊዜ እናቶቻቸውን “እቅፍ አድርገው እንደሚስሙ” ተናግረዋል። በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች “እወድሻለሁ” እና “አመሰግንሻለሁ” ማለትን ነው።

በቡልጋሪያ የተደረገ የደም ሴሚናር

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በሶፍያ፣ ቡልጋሪያ በቀዶ ሕክምና ወቅት ብዙ ደም እንዳይፈስ ስለሚደረግ ጥንቃቄና የደም ምትክ የሆኑ መድኃኒቶችን ስለመጠቀም አንድ ሴሚናር ተደርጎ ነበር። ይህ ሴሚናር ከመላዋ ቡልጋሪያ የተሰባሰቡ ዶክተሮች ከስምንት የተለያዩ አገሮች ከመጡ የደም ኤክስፐርቶች ጋር ለመነጋገር አጋጣሚ አስገኝቶላቸዋል። የሶፍያው ፕሮፌሰር ኢቫን ምላዲኖቭ በቀድሞው መንግሥት ዘመን ‘ስለ ደም መበከልም ሆነ በደም አማካኝነት ስለሚተላለፉ ቫይረሶች’ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በተጨማሪም ‘በሽተኞች የሚያቀርቡት ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ እንደ መጥፎ ምግባር ስለሚታይ የሕክምና እርዳታ እስከመነፈግ ያደርስ ነበር’ ብለዋል። በሴሚናሩ ላይ የተገኙት ዶክተሮች በቡልጋሪያ በአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ስለ ጸደቀው በሽተኛው ስለሚደረግለት ሕክምና በራሱ የመወሰንና አውቆ የመስማማት መብት ተጨማሪ ግንዛቤ ሊገኝ እንደቻለ ገልጸዋል።

የስፔይን ልጆችና ቴሌቪዥን

በስፔይን አገር አንድ ቴሌቪዥን የሚመለከት ሕፃን የአሥር ዓመት ዕድሜ ሲሞላው በአማካይ 10,000 ግድያዎችና 100,000 ድብድቦች ሲፈጸሙ ለመመልከት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት የስፔይን ኮሚቴ ባልደረባ የሆኑት ካርሎስ ማርያ ብሩ እንደተናገሩ ዩሮፓ ፕሬስ ዘግቧል። በተጨማሪም ከ4 እስከ 12 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የስፔይን ሕፃናት መካከል ሦስት አራተኛ የሚሆኑት በቀን ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ሰዓት ተኩል ቴሌቭዥን እንደሚመለከቱና አንድ አራተኛ የሚሆኑት ደግሞ በየቀኑ ከአራት ሰዓት በላይ እንደሚያዩ ፕሮፌሰር ሉዊስ ሚገል ማርቲኔዝ ገልጸዋል። ልጆች በአማካይ “በዓመት ውስጥ 937 ሰዓት ያህል ቴሌቪዥን በመመልከት የሚያሳልፉ ሲሆን ይህም በየዓመቱ በትምህርት ከሚያሳልፉት 900 ሰዓት እንደሚበልጥ” ሪፖርቱ ያመለክታል። በኮምፑሊቴኔዥያን ዩኒቨርሲቲ የመረጃ ሳይንስ ክፍል ባልደረባ የሆኑት ፔሬዝ አዝናር እንደሚሉት በኅብረተሰቡ ውስጥ የኃይል ድርጊት እንዲስፋፋ ከሚያደርጉት ማኅበረሰባዊ ሁኔታዎች አንዱ በቴሌቪዥን ላይ የሚታይ የኃይል ድርጊት ነው።

የቻይና ታሪክ የበለጠ ዕድሜ እንዳለው ታወቀ

የቻይና በጽሑፍ ላይ የሠፈረ ታሪክ የምዕራብ ቹ ሥርወ መንግሥት ወራሽ ከነበሩት ከጎ ሂ አንደኛ ዘመነ መንግሥት፣ ከ841 ከዘአበ እንደማያልፍ ይታመን ነበር። በቅርቡ ግን ስለ አንድ የፀሐይ ግርዶሽ የሚጠቅስ ከዚህ የበለጠ ዕድሜ ያለው መዝገብ እንደተገኘ ቻይና ቱ ዴይ ዘግቧል። ይህ መዝገብ ግርዶሹ የታየው የቹ ሥርወ መንግሥት አባል የሆኑት ንጉሥ ዪ በነገሡበት የመጀመሪያ ዓመት እንደሆነ ያመለክታል። የሳይንስና የታሪክ ተመራማሪዎች ይህ ግርዶሽ የታየው በ899 ከዘአበ እንደነበረ ስላረጋገጡ የቻይና ታሪክ በጽሑፍ መስፈር የጀመረበት ዘመን ከግማሽ መቶ ዓመት በላይ ወደ ኋላ ተመልሷል። አውትላይን ኦቭ ዘ ሂስትሪ ኦቭ ዘ ቻይኒዝ ፒፕል የተባለው መጽሐፍ “ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ 20ኛው መቶ ዘመን ድረስ የቻይና የታሪክ መዝገብ አንድ ጊዜ እንኳን አልተቋረጠም” ይላል። ይህ መዝገብ “ቻይናውያን ለሰው ልጅ የሥልጣኔ ታሪክ ካበረከቷቸው ታላላቅ አስተዋጽኦዎች አንዱ ነው” ይላል።

ሙዚቃ በሸማቾች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል

በእንግሊዝ አገር ከላይሰስተር ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ የሥነ ልቦና ምሁራን በንግድ ቤቶች የሚሰማ ሙዚቃ የወይን ሸማቾች በሚያደርጉት ምርጫ ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር አረጋግጠዋል። “የፈረንሳይ የአኮርድዮን ሙዚቃ በሚሰማበት ጊዜ የፈረንሳይ ወይን ጠጆች ከጀርመኖቹ አምስት ጊዜ እጥፍ ተሽጠዋል” ይላል ናሽናል ጂኦግራፊክ መጽሔት። “የጀርመን መሸታ ቤቶች ሙዚቃ በሚደለቅበት ጊዜ ሸማቾች የገዟቸው የጀርመን ወይን ጠጆች ከፈረንሳዮቹ በሁለት እጥፍ በልጧል።” የሚያስገርመው “ባደረጉት ምርጫ ላይ ሙዚቃ ተጽእኖ እንዳሳደረባቸው የተገነዘቡት ጥቂቶቹ ናቸው” በማለት ከተመራማሪዎቹ አንዱ ተናግሯል።

ላሞችም ይመቻቸው

በአሮጌ ጎማ ቁርጥራጮች የተሞሉ ፍራሾች በከብቶች በረት ውስጥ መታየት እንደጀመሩ የካናዳው ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል ዘግቧል። የአምስት ሴንቲ ሜትር ውፍረት ያለው ፍራሽ ላሞች ብዙ ወተት እንዲሰጡና የሚታለቡባቸውንም የጊዜ ርዝመት እንደሚጨምር ይታሰባል። በዚህ ዘገባ መሠረት “የወተት ላሞች አብዛኛውን የሕይወት ዘመናቸውን የሚያሳልፉት በሲሚንቶ ወለል ላይ ነው። በዚህም ምክንያት ሸኮናቸው ይቆስላል፣ ጉልበታቸውም ይጎዳል።” ፍራሾቹ በከብቶቹ እግርና ጉልበት ላይ የሚደርሰውን ችግር ከመቀነሳቸውም በላይ ዘፍ ብለው በሚተኙበት ጊዜ በጉልበታቸው ላይ የሚደርሰውን ምት ይቀንሳሉ። አንድ የፍራሾቹ አምራች ዓላማችን ላሞቹ በሣር ግጦሽ ላይ ሲተኙ የሚሰማቸው ዓይነት ምቾት እንዲሰማቸው ማድረግ ነው ይላል።

በጥላ ውስጥም ቆዳ ሊቃጠል ይችላል

የአውስትራሊያ ክዊንስላንድ የሕክምና ምርምር ተቋም ያደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው ዛፍ ወይም ጃንጥላ ሥር መጠለል ከልዕለ ሐምራዊ ጨረር ሙሉ በሙሉ ላያድነን ይችላል። ዘ ካንቤራ ታይምስ ላይ የወጣው ይህ ሪፖርት ክፍት በሆነ ጥላ ውስጥ የሚቀመጥ ሰው ለተሠራጩ የልዕለ ሐምራዊ ጨረሮች መጋለጡ አይቀርም። ባዮኬሚስትና የዚህ ጥናት ተባባሪ ጸሐፊ የሆኑት ዶክተር ፒተር ፓርሰንስ እንደሚከተለው በማለት አስጠንቅቀዋል:- “በሁሉም የአውስትራሊያ ዋና ከተሞች ለእኩለ ቀን የበጋ ፀሐይ በቀጥታ የመጋለጥ ወሰን ከ10 እስከ 12 ደቂቃ ቢሆን በጥላ ውስጥ የተኙ ወይም የቆሙ ሰዎች ከአንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቆዳቸው በልዕለ ሐምራዊ ጨረሮች ይቃጠላል።” በክረምትና በደመና ቀኖች እንኳን ከፍተኛ መጠን ያለው ልዕለ ሐምራዊ ጨረር በአካባቢያችን ይኖራል። “ለሰማይ ይበልጥ በተጋለጥክ መጠን የሚደርስብህም አደጋ በዚያው መጠን ይጨምራል” በማለት ዶክተር ፓርሰንስ ያሳስባሉ።

ብክለት በመኪና አሽከርካሪዎች ላይ የሚያሳድረው አደጋ

“በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት መኪናው ውስጥ ተቀምጦ ለመቆየት የተገደደ አንድ አሽከርካሪ በዚህ ጊዜ የሚተነፍሰው የተበከለ አየር አንድ ብስክሌተኛ ወይም እግረኛ ከሚተነፍሰው በሦስት እጥፍ፣ በአውቶቡስ ከሚጓዝ ሰው በሁለት እጥፍ ይበልጣል” ሲል የለንደኑ ዘ ታይምስ ዘግቧል። የአውሮፓ የአካባቢ ፖሊሲ ተቋም ያደረገው ጥናት በአውራ ጎዳና መሐል በተጨናነቀ ትራፊክ ውስጥ የሚያዘግሙ አሽከርካሪዎች “በጣም ብዙ መርዛማ አየር” እንደሚተነፍሱ አመልክቷል። የአካባቢ ሁኔታ ተሟጋች የሆኑት አንድሩ ዴቪስ እንዳሉት የመከላከያ ጭንብል ማድረግ ይበልጥ አስፈላጊ የሚሆነው ብዙ ጊዜ እንደሚታሰበው ወደ ዳር ወጣ ብለው ለሚጠባበቁ ብስክሌተኞች ሳይሆን ለመኪና አሽከርካሪዎች ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ