የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g99 5/8 ገጽ 3-4
  • ስለ ሃይማኖት ትወያያለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስለ ሃይማኖት ትወያያለህን?
  • ንቁ!—1999
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አለመቻቻል ብዙዎችን ተስፋ ያስቆርጣቸዋል
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የእውነተኛ ሃይማኖት ዘላለማዊ ጌጦች
    ንቁ!—1998
  • ለደህንነት በሚያበቃ ንጹሕ ሃይማኖት መመላለስ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ሃይማኖት ሊወያዩበት የማይገባ ርዕስ ነውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1999
g99 5/8 ገጽ 3-4

ስለ ሃይማኖት ትወያያለህን?

“ርዕሳችንን ብንቀይር ይሻላል። ስለ ሃይማኖትና ስለ ፖለቲካ መወያየት አልወድም!”

“ሃይማኖት ለሴቶችና ለልጆች የተተወ ነው።”

“ከቤተ ክርስቲያን ገና መመለሴ ስለሆነ አሁን ስለ ሃይማኖት መወያየት አልፈልግም።”

እነዚህ አስተያየቶች የተለመዱ ናቸው? አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖት በእነሱና በአምላክ መካከል የተወሰነ ጉዳይ እንደሆነ አድርገው ስለሚያስቡ ስለ ሃይማኖት መወያየት አይፈልጉም። ኢየሱስ ራሱ “ስትጸልይ፣ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል” ብሏል።—ማቴዎስ 6:6

በሌላ በኩል ግን ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ሁሉም የሃይማኖት ገጽታ የግል ጉዳይ መሆን አለበት የሚል እምነት አልነበራቸውም። ስለተለያዩ መንፈሳዊ ርዕሶች በነፃነትና በግልጽ ይናገሩ ነበር። ይህም ትምህርታቸው በዓለም ዙሪያ እንዲሰራጭ አስተዋጽኦ አድርጓል። (ሥራ 1:8፤ ቆላስይስ 1:23) እርግጥ ነው፣ የሚያገኙት ሰው ሁሉ ከእነርሱ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ ይሆን ነበር ማለት አይደለም። በጥርጣሬ ዓይን መመልከት የመረጡም ነበሩ።

በዛሬው ጊዜም ስለ ሃይማኖት መወያየትን በተመለከተ ያለው አመለካከት ከሰው ወደ ሰው እንዲሁም ከባሕል ወደ ባሕል ይለያያል። ለምሳሌ ያህል በብዙ ምዕራባውያን አገሮች ሰዎች እንደ ትምህርት፣ ሥራ፣ ስፖርት፣ ኮምፒዩተሮችና ቴሌቪዥን በመሳሰሉ ሰብዓዊ ጉዳዮች የመጠመድ አዝማሚያ ይታይባቸዋል። በሌሎች ኅብረተሰቦች ደግሞ ሰዎች ስለ እምነታቸው ለመወያየት ይበልጥ ፈቃደኞች ናቸው። ሆኖም ቀደም ሲል ለሃይማኖት ግድ ያልነበራቸው አንዳንድ ሰዎች አስተዳደጋቸው ምንም ይሁን ምን በሕይወታቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸው ነገሮች ቆም ብለው ስለ መንፈሳዊ ፍላጎታቸው እንዲያስቡ ይገፋፏቸዋል።

አለመቻቻል ብዙዎችን ተስፋ ያስቆርጣቸዋል

ስለ ሃይማኖት ለመወያየት ፈቃደኛ የማይሆኑ ሰዎች ከዚህ ቀደም ወደ ጦፈ ክርክር የተለወጠ ውይይት ሲካሄድ ተመልክተው ሊሆን ይችላል፤ አለዚያም ደግሞ ራሳቸው በእንዲህ ዓይነቱ ውይይት ተካፍለው ይሆናል። በንግግር ችሎታቸው ዝናን ያተረፉ አንድ ሰው “ከፖለቲካ ልዩነት ይልቅ የሃይማኖት ልዩነት ወደ ከፋ ጠብ ይመራል” ሲሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሪቻርድ ኤም ጆንሰን እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል:- “ሃይማኖታዊ ቅንዓት በሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ወገናዊ ጥላቻ እንዲጠነሰስ ያደርጋል። አግባብ ባልሆነ መንገድ ሲሠራበት ደግሞ በአምላክ አገልግሎት ሽፋን ከሁሉ የከፋ ድርጊት ወደ መፈጸም ያደርሳል።”

በእጅጉ ሊገነቡና ሊያጎለምሱ የሚችሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች አለመቻቻልን፣ ወገናዊነትንና ጥላቻን ለማራመድ አግባብ ባልሆነ መንገድ ጥቅም ላይ መዋላቸው አስገራሚ ሆኖብሃልን? እርግጥ ብዙዎች ሃይማኖትን እንዲጠሉ ያደረጓቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ሳይሆኑ እነዚህ ትምህርቶች በትክክል ተግባራዊ አለመደረጋቸው ነው። ለምሳሌ ያህል ክርስትናን ተመልከት።

የክርስትና መሥራች የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎች አለመቻቻልንና አክራሪነትን ከማንጸባረቅ ይልቅ አምላክንና ሰውን እንዲወዱ በቃልም ሆነ በድርጊት አበረታቷል። ክርስቶስም ሆነ ተከታዮቹ በአገልግሎታቸው ሰዎችን ያነጋግሩ የነበረው በማስረዳትና አሳማኝ ምክንያት በማቅረብ ነበር። (ማቴዎስ 22:41-46፤ ሥራ 17:2፤ 19:8) በተጨማሪም ለጠላቶቻቸውና ለአሳዳጆቻቸው ይጸልዩ ነበር።—ማቴዎስ 5:44፤ ሥራ 7:59, 60

እውነተኛ ሃይማኖት የአእምሮንና የልብን የእውቀት አድማስ ያሰፋል። ሰዎችንም አንድ ያደርጋል። እንግዲያው ቀጥሎ እንደምንመለከተው እውነትን ከልባቸው ለሚፈልጉ ሰዎች ረጋ ባለ መንፈስ የሚካሄድ ሃይማኖታዊ ውይይት ፍሬያማ ሊሆንላቸው ይችላል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የታላላቅ ሰዎች ጥቅሶች

“ወደ አምላክ የሚያደርሰው መንገድ ኢየሱስ ከሆነ የኢየሱስ ተከታዮች ይህን እውቀት ለሌሎች ሰዎች የግድ ማካፈል ይኖርባቸዋል።”—ቤን ጆንሰን፣ በኮሎምቢያ ቲኦሎጂካል ሴሚኔሪ የወንጌላዊነት ፕሮፌሰር።

“ኢየሱስ ወንጌልን ለሰዎች እንዲያደርሱ ደቀ መዛሙርቱን አስተምሯቸዋል። ይህ ታላቅ ተልዕኮ ወደ ሁሉም የዓለም ክፍሎች እንድንሄድ ያስገድደናል። ጌታ በሁሉም ቦታ እንዲያዳርሱ ተከታዮቹን አዝዟል።”—ኬኔት ኤስ ሄምፕሂል፣ የቸርች ግሮውዝ የደቡባዊ መጥምቃውያን ማዕከል ዲሬክተር።

“ምሥክሮች ካልሆንን እውነተኛ ክርስቲያኖች ልንሆን አንችልም። ... እያንዳንዱ ክርስቲያን ሚስዮናዊና ምሥክር መሆን አለበት።”—ሊቀ ጳጳስ ጆን ፖል ዳግማዊ።

“ብዙ ሰባኪዎች . . . ለአንዳንዶች የማይዋጥላቸውን በወንጌል ውስጥ የሚገኘውን መልእክት ሳይበርዙ ሳይከልሱ ከመስበክ ይበልጥ የሚያሳስባቸው ነገር ትልልቅ ጉባኤዎችን መመሥረትና የቤተ ክርስቲያን የግንባታ ፕሮጀክቶችን ማካሄድ እንዲሁም የሚቀጥለው የቅስና ምድባቸው ነው።”—ካል ቶማስ፣ ደራሲና የመጽሔት አምድ አዘጋጅ።

“እንደ (የይሖዋ) ምሥክሮችና እንደ አንዳንዶች ... ከቤት ወደ ቤት መሄድ አለብን። እዚያው ድረስ ሄደን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማወጅ አለብን።”—ቶማስ ቪ ዴይሊ፣ የካቶሊክ ጳጳስ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ