የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 12/1 ገጽ 31
  • የሚችሉትን ያህል ያደርጋሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሚችሉትን ያህል ያደርጋሉ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ”
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ለምታሳዩት ፍቅር ይሖዋን እናመሰግናለን
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የሁሉም ነገር ባለቤት ለሆነው አምላክ ምን ልንሰጠው እንችላለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • “የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ”
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 12/1 ገጽ 31

የሚችሉትን ያህል ያደርጋሉ

ብዙ ሰዎች ይሖዋ ላደረገላቸው ሁሉ ውለታውን መክፈል ባይችሉም ዓለም አቀፉን የምሥክሮች የስብከት ሥራ ለመደገፍ የተቻላቸውን ያህል ያደርጋሉ። (ማቴዎስ 24:14፤ ከማርቆስ 14:3-9 ጋር አወዳድር) ይህ ከሚኔሶታ ዩ.ኤስ.ኤ ከሚኖር ቤተሰብ የተላከ ደብዳቤ ትኩረታችንን የሚስብ ነው።

“ውድ ወንድሞች

“መጠኑ--የሆነ ዕርዳታ ልከንላችኋል። ለዓለም አቀፉ ሥራ ወጪ እንዲውል ወይም ለመንግሥት አዳራሽ መሥሪያ እንዲሆን ወይም ድርጅቱ ለሚያስፈልገው ለማንኛውም ጉዳይ እንዲውል እንጠይቃለን።

“ይህ ገንዘብ (ከይሖዋ) ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ መንገድ እንደሚሠራበት እርግጠኞች ነን። በዚህ አጋጣሚ በመልካሙ ሥራችሁ እንድትቀጥሉ እናበረታታችኋለን። በተለይም (የመጠበቂያ ግንብ) ማኅበርን ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ የሚያሳየውን ቪዲዮ ቴፕ ስላዘጋጃችሁ ምስጋናችንን ልንገልጽ በጣም ደስ ይለናል። የሥራውን ከፍተኛነት ያስገነዘበን ይህ ቴፕ ነበር። በፈቃደኛነት የምንሰጠው እርዳታችን አስፈላጊ እንደሆነም ጠቁሞናል። ከዚህ በፊት የእርዳታውን ገንዘብ ለእናንተ የመላኩን ሥራ ለጉባኤው፣ ለክልሉና ለወረዳው ትተን ነበር። ይሖዋ አርቀን አለማየታችንን ታግሶ ከሌላ የዕርዳታ መስኮት በተጨማሪ የዚህን ሕይወት አድን ሥራ ወጪ ለመሸፈን በግላችን እርዳታ የማድረግን አስፈላጊነት በፍቅራዊ መንገድ ስላሳየን እናመሰግነዋለን። በቤተሰብ መልክ በየወሩ ቢያንስ ቢያንስ ብር — — በቀጥታ ወደ ኒውዮርክ ለመላክ ወስነናል።

“ላደረጋችሁልን መልክም አገልግሎትና ለይሖዋ ስለምታሳዩት ታማኝነት እንደገና እናመሰግናችኋለን።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ