በታኅሣሥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር
1 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የምሥራቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ አዟቸዋል። (ማቴ. 28:19, 20) ሌሎችን ማስተማር የምንችልበት ዋነኛው መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በመምራት ነው። በዚህ ሥራ እየተካፈልክ ነውን? ካልሆነ ሌሎችን በማስተማሩ ሥራ የበለጠ መካፈል ትቸል ዘንድ ጥናት መጀመር የምትችለው እንዴት ነው?
2 ምናልባት ለቤቱ ባለቤት ትራክት ሰጥተነው በውስጡ ያሉትን ሐሳቦች ለመወያየት ተመልሰን ሄደን እንደምንጠይቀው ነግረነው ይሆናል።
“ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆን?” የሚለውን ትራክት ያበረከትንለትን የቤት ባለቤት ተመልሰን ስንጠይቅ እንዲህ ለማለት እንችላለን፦
◼ “ከጥቂት ቀናት በፊት መጥቼ በነበረበት ጊዜ ስለ ጊዜያችን አጣዳፊነት እንዲሁም ባለንበት ጊዜ ምን ዓይነት ሁኔታዎች እንደሚከሰቱ ኢየሱስ በትክክል የተናገረ መሆኑን ተወያይተን ነበር። ትቼለዎት ከሄድኩት ትራክት ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል አጠር አድርገን አንዳንድ ሐሳቦችን ብንወያይ ደስ ይለኛል። ‘ምልክቱ’ በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር ምን እንደተጠቀሰ ልብ ይበሉ።” የትራክቱን ገጽ 3 አውጣና ጊዜ በፈቀደልህ መጠን በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር ያሉትን ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን ጥቅሶች እያነበብክ የመጀመሪዎቹን ሁለት ወይም ሦስት አንቀጾች አወያየው። ዛሬ፣ ኢየሱስ የተናገረው ትንቢት እንዴት በመፈጸም ላይ እንዳለ አጉላ። በዚህ ንዑስ ርዕስ ሥር ባሉት ሌሎች አንቀጾች ላይ ለመወያየት ተመልሰህ ለመሄድ ዝግጅት አድርግ። ተመልሰህ ከመሄድህ በፊት የቤቱ ባለቤት ትምህርቱን እንዲያነበው አበረታታው።
3 ወይም እንዲህ ለማለት ትቸላለህ፦
◼ “ባለፈው ጊዜ ስንነጋገር ይህ ዓለም ከመጥፋት ይተርፍ ይሆን? የምትለዋን ትራክት ሰጥቼዎት ነበር። ያኔ ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለም ጉዳዮች ላይ ያለውን ሚና በተመለከተ ተነጋግረን ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዮሐንስ 17:3 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የእርሱ ቃል እንዲህ ይነበባል። [አንብብ] የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ከፈለግን ስለ አምላክና ስለ ኢየሱስ ማወቅ አስፈላጊ ስለሆነ ይህን እውቀት ለማግኘት የምንችለውን ሁሉ ማድረጋችን ተገቢ ነው። ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ብዙ የአምላክን አስደሳች ባሕርያት አንጸባርቋል። ታዲያ ስለ ኢየሱስና እርሱ ስላከናወነው አገልግሎት የበለጠ ባወቅን መጠን ስለ አባቱ የበለጠ እናውቃለን ብሎ ማመኑ ምክንያታዊ አይደለምን? [መልስ እንዲሰጥ ፍቀድለት።] እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለው ይህ መጽሐፍ የሚለውን ልብ ብለው ያስተውሉ።” በምዕራፍ 116 በአሥረኛው ገጽ ላይ ያሉትን አንደኛውንና ሁለተኛውን አንቀጾች አንብብ። ይህ መጽሐፍ ስለ ኢየሱስ በአራቱም ወንጌሎች ላይ የተዘገቡትን ማብራሪያዎች ሁኔታዎቹ በተፈጸሙበት ቅደም ተከተል መሠረት ሁሉንም መረጃዎች ይዟል። የተወሰኑ ምዕራፎችን ርዕስ፣ ሥዕላዊ መግለጫዎችንና በመጽሐፉ መጀመሪያ ላይ ያለውን ካርታ አሳየው። መጽሐፉን እንዲወስድ በመጋበዝ አቅርብለት።
4 “ታላቁ ሰው” የተባለውን መጽሐፍ ለወሰደ የቤት ባለቤት ሰላምታ ካቀረብክ በኋላ እንዲህ ልትል ትቸላለህ፦
◼ “ባለፈው ጊዜ መጥቼ ሳለ እንደጠቀስኩት ታላቁ ሰው የተባለው መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት እንዲረዳ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። መጽሐፉን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዴት አድርጎ መጠቀም እንደሚቻል ባሳየዎት ደስ ይለኛል።” “ከሰማይ የመጣ መልእክት” የሚለውን የመጽሐፉን ምዕራፍ 1 አውጣ። የቤቱ ባለቤት ትኩረቱን በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ ወዳሉት ጥያቄዎች እንዲያዞር አድርግ። የመጀመሪያውን ጥያቄ አንብብ። ከዚያም በመጀመሪያዎቹ አንቀጾች ላይ አወያየው። ውይይቱን በሁለተኛው ገጽ ላይ ካለው ሥዕል ጋር አያይዘው። የቀሩትንም ጥያቄዎች ተወያዩባቸውና ጊዜ በፈቀደልህ መጠን መልሶቹን አጉላ። ከመደምደምህ በፊት ተመልሰህ በመሄድ ውይይቱን ለመቀጠል ዝግጅት አድርግ።
5 ይሆናል የሚል አመለካከት በመያዝ፣ በደንብ በመዘጋጀትና እያንዳንዱን አጋጣሚ በመጠቀም በታኅሣሥ ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር በሚገባ የታጠቅን እንሆናለን።