የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/94 ገጽ 2
  • የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • የካቲት 7 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 14 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 21 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 28 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 2/94 ገጽ 2

የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች

የካቲት 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 19

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታቸን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በጥያቄ ሳጥን ውስጥ ያሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ከልስ።

18 ደቂቃ፦ “ሰዎች በአምላክ የሰላም መንግሥት ላይ ያላቸውን ፍላጎት አሳድግ” ትምህርቱን ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ሁለት ትዕይንቶችን አቅርብ። ሁለተኛውን አንቀጽ ካብራራህ በኋላ በሥራ ለተጠመደ የቤት ባለቤት እንዴት ትራክት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ትዕይንት አቅርብ። አስፋፊው ለተመላልሶ መጠይቅ መሠረት ለመጣል የሚያስችለውን ጥያቄ በአክብሮት ያቅርብ። በአንቀጽ 3 ላይ የሚገኘውን አቀራረብ በመጠቀም ፍላጎት ያሳየን የቤት ባለቤት አንድ አስፋፊ ለዘላለም መኖር በተባለው መጽሐፍ ሲያነጋግረው የሚያሳይ ትዕይንት አቅርብ። አሁንም ለተመላልሶ መጠይቅ መሠረት መጣል አለበት።

12 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ይህንን ጊዜ በ“መለኮታዊ ትምህርት” የወረዳ ስብሰባ ላይ የተደረጉትን ፕሮግራሞች በከለሰበት ሳምንት ጉባኤው ያመለጡትን ነጥቦች በመሸፈን ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።

መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ማኅበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት የምስጋና ደብዳቤ ካለ ግለጽ፤ እንዲሁም የጉባኤውን አስፈላጊ ወጪዎች ለመሸፈን ለሚያደርጉት የታማኝነት ድጋፍ ጉባኤውን አመስግን። ቅዳሜና እሁድ በሚደረገው የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ አበረታታቸው።

20 ደቂቃ፦ “ትርጉም ያላቸው ተመላልሶ መጠይቆችን በማድረግ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች እድገት እንዲያደርጉ ማነቃቃት።” በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት። በአንቀጽ ሁለት ላይ ባለው አቀራረብ መሠረት ተመላልሶ መጠይቅ ሲደረግ የሚያሳይ አንድ ትዕይንት አቅርብ። ተመልሰን በምንጎበኛቸው ጊዜ ብዙ ነጥብ ከመሸፈን ይልቅ ወደፊት ለሚደረገው ጉብኝት ፍላጎት እንዲያድርባቸው ማድረግ እንዳለባቸው አጥብቀህ ግለጽ።

15 ደቂቃ፦ “የሰዎችን ትኩረት ወደ ድርጅቱ መሳብ።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በግለት የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 155 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 105

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “የይሖዋን በኩር በእልልታ ተቀበል!” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን ትምህርት። ለመታሰቢያው በዓልና በሚቀጥሉት ጊዜያት ለሚደረጉት ቋሚ ንግግሮች የሚጋብዟቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር እንዲጽፉ ሁሉንም በማበረታታት ሞቅ ባለ ስሜትና በግለት በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በአንቀጽ 7 ላይ ያሉትን ነጥቦች በትዕይንት አቅርብ። በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ገብቶ ግራና ቀኝ በዓይኑ የሚያማትርን ሰው አንድ አስፋፊ ቀርቦ እንዲያናግረው አድርግ። ሰውዬው በሌላ ከተማ የሚኖሩ ዘመዶቹ አበረታትተውት ወደ እዚያ እንደመጣ ለአስፋፊው ይገልጽለታል። አስፋፊውም ከእርሱና ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀመጥና መጽሐፍ ቅዱስና የመዝሙር መጽሐፍ አብሯቸው እንዲመለከት ይጋብዘዋል። ከስብሰባው በኋላ ጥያቄ ካለው እንዲጠይቅ ይጋብዘዋል። በመደምደሚያህ ላይ ጉባኤው የሞቱን መታሰቢያ በዓል መቼ እንደሚያክበር አስተዋውቅ።

10 ደቂቃ፦ መጽናኛ ለማግኘት ከሁሉ የተሻለ ምንጭ የሚሆንልን — መጽሐፍ ቅዱስ። ምክንያቱን ማስረዳት ከገጽ 117–21። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በጉባኤ ውስጥ ያሉትም ሆኑ በውጪ ያሉት ብዙዎቹ ሰዎች ማጽናኛ ያስፈልጋቸዋል። በጉባኤ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ አስፋፊ ሌሎችን ለማጽናናት በአምላክ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ እንዴት መጠቀም እንደሚችል አሳይ።

15 ደቂቃ፦ ‘በአሕዛብ ሁሉ የተጠሉ።’ ችሎታ ባለው ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

መዝሙር 191 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

የካቲት 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 174

8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። በቅርብ በታተሙ መጽሔቶች በመጠቀም መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል በትዕይንት አሳይ።

12 ደቂቃ፦ “የሰዎችን ትኩረት ወደ ድርጅቱ መሳብ”። በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከተመራ በኋላ ‘የይሖዋ ምስክሮች’ በሚለው በአዲሱ ብሮሹራቸን ገጽ 14 ላይ ባሉት የመጀመሪያ ሁለት አንቀጾች በመጠቀም ውይይት ሲደረግ የሚያሳይ አምስት ደቂቃ የሚፈጅ ትዕይንት አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “የጉባኤያችሁን ሕዝባዊ ስብሰባ ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ ደግፉ።” በንግግር የሚቀርብ ሆኖ ለአድማጮች አንድ ወይም ሁለት ጥያቄዎችን ማቅረብ ይቻላል። ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝባዊ ስብሰባዎች ላይ የተገኙ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ጥሩ አቀባበል እንደተደረገላቸው እንዲሰማቸው ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ግለጽ። በቅድሚያ የተዘጋጀ አንድ አስፋፊ አዘውትሮ በሕዝብ ስብሰባ ላይ በመገኘቱ እንዴት እንደተጠቀመ እንዲናገር አድርግ።

10 ደቂቃ፦ “የተሳሳተ ደግነት ከማሳየት ተጠበቁ።” በንግግር የሚቀርብ።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ