የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/94 ገጽ 5-6
  • ‘የሰዎችን ትኩረት ወደ ድርጅቱ መሳብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የሰዎችን ትኩረት ወደ ድርጅቱ መሳብ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአዲሱ ብሮሹር አጠቃቀም
  • በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ መጠቀም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ማንበብና ያነበቡትን ማስታወስ የሚቻልበት መንገድ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • ለትምህርታችሁ የማያቋርጥ ትኩረት ስጡ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ሌሎች ሰዎች ስለ ታላቁ ሰው እንዲማሩ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 2/94 ገጽ 5-6

‘የሰዎችን ትኩረት ወደ ድርጅቱ መሳብ

1 በእውነት ውስጥ ያሳለፋችሁት የራሳችሁ ተሞክሮ የተስተካከለ መንፈሳዊ እድገት እንድናደርግና በእምነት ተደላድለን እንድንቆም የጉባኤ ዝግጅት ምን ያህል እንደሚያስፈልገን እንድትገነዘቡ እንደረዳችሁ ምንም አያጠራጥርም። (ዕብ. 10:24, 25) ይህ ደግሞ ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችሁ መሠረተ ትምህርት ነክ የሆኑትን ነገሮች በግልጽ እንዲረዱ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይሖዋ እየተጠቀመበት ስላለው ድርጅት ተመሳሳይ የሆነ ጥልቅ አድናቆት እንዲኖራቸው ለመርዳት በጥብቅ እንድታስቡ ያደርጋችኋል። (ሉቃስ 6:40) ይህን ለማድረግ እንደ አንድ አካል ሆነው የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምስክሮች የሚለው አዲሱ የአማርኛ ብሮሹራችን ሊረዳችሁ ይችላል።

2 ጥናት የጀመሩ ሰዎች የይሖዋ ድርጅት መዋቅርና አሠራር በቅዱሳን ጽሑፎች ላይ የተመሠረተ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋቸዋል። እድገት እንዲያደርጉ ከተፈለገ ከአንድ ሌላ አዲስ ሃይማኖት ጋር እየተዋወቁ እንዳሉ ብቻ ሳይሆን የይሖዋ መንገዶች በድርጅቱ በኩል ሲንጸባረቁ ጥልቀት ባለው መንገድ በማስተዋል ላይ መሆናቸውንም መረዳት አለባቸው።

የአዲሱ ብሮሹር አጠቃቀም

3 ጥናት ለመጀመር ዝግጅት ሲደረግ ተማሪው የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምስክሮች የተባለው ብሮሹር አንድ ቅጂ ሊሰጠውና የሳምንታዊ ጥናቱ ክፍል እንደ አንዱ የሆነው የትኛው ርዕስ እንደሆነ በቅድሚያ ሊነገረው ይገባል። እንዲህ ከሆነ ለጥናቱ ተዘጋጅቶ ሊመጣ ይችላል። በምትዘጋጅበት ጊዜ ተማሪው ቀድሞ የነበረበትንም ሆነ አሁን ያለበትን ሃይማኖት በአእምሮህ በመያዝ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ ከተመሠረተው የይሖዋ ድርጅት ጋር ያለውን ልዩነት በትምህርቱ ወቅት በተሻለ ሁኔታ ልታጎላለት ትችላለህ። ብዙውን ጊዜ በማነጻጸር የሚሰጥ ትምህርት በተማሪው አእምሮ ውስጥ ልዩነቱን በግልጽ ለማስቀመጥ ይረዳል። ቁልፍ ጥቅሶችን እያወጣችሁ ተመልከቷቸው። በአብዛኛዎቹ የብሮሹሩ 15 ምዕራፎች መካከል መጨረሻ ላይ በሚገኙት የክለሳ ጥያቄዎች ተጠቀም። በዚህ መንገድ ግለሰቡ ስለ ይሖዋ ድርጅት ይበልጥ ግልጽ የሆነ አመለካከት እንዲይዝ ትረዳዋለህ።

4 ለምሳሌ ያህል “በፍቅርና በአንድነት የሚገነቡን ጉባኤዎች” በሚለው ርዕስ ስር ያለውን ክፍል ስትሸፍን ተማሪውን እርሱ ባለበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት የሃይማኖት መሪዎች ምን ዓይነት ሥልጣን እንደሚሰጣቸውና እንዴት እንደሚታዩ ልትጠይቀው ትችል ይሆናል። ከዚያም በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ከሚታየውና ከሚደረገው ነገር ጋር ቅዱስ ጽሑፋዊ በሆነ መንገድ በመመርመር ከሌሎች ፈጽሞ የተለየ መሆኑን በመግለጽ ልትቀጥል ትችላለህ። እንዲሁም በገጽ 28 ላይ የሚጀምረውን ሥራው እንዴት በገንዘብ እንደሚደገፍ የሚያብራራውን ክፍል በምትሸፍንበት ጊዜም ተመሳሳይ አቀራረብ መጠቀም ትችላለህ። ይህ ተማሪው የይሖዋን መንገድ እንዲያደንቅና አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ሊያነሳሳው ይችላል።

5 በአንዱ ክፍል ውስጥ ያለውን ሁሉንም ነጥብ የግድ በአንድ የጥናት ክፍለ ጊዜ ውስጥ መሸፈን እንደሌለብህ አስብ። እንደ ክፍሉ ርዝመት ለሁለትና ለሦስት የጥናት ጊዜ ልትከፋፍለው ትችላለህ። ለተወያያችሁበት ነጥብ ተስማሚ የሆኑትን የክለሳ ጥያቄዎች በመጠቀም በተወያያችሁበት ክፍል ውስጥ የሚገኙትን ነጥቦች ለማጉላት ሁልጊዜ ከጥናቱ በኋላ አምስት ወይም አስር ደቂቃ ብቻ መመደብ ሊበቃ ይችላል።

6 የጥቅሱን ሃሳብ በተማሪው አእምሮ ውስጥ አጠናክረው ለመቅረጽ በሚያገለግሉት ሥዕሎችና ምሳሌዎች ተጠቀም። ብዙዎቹ ሥዕሎች የይሖዋን ድርጅት ዓለም አቀፋዊ የወሰን ክልል እንዲሁም የዘር፣ የአስተዳደግ፣ ወይም የብሔር ልዩነት የሌለበትን በአምላክ ሕዝቦች መካከል የሰፈነውን አንድነት በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው። ኢየሱስ በዓለም ዙሪያ ወንጌሉ እንዲሰበክ የሰጠውን ተልእኮ ሊፈጽም የሚችለው እንዲህ ዓይነቱ ድርጅት ብቻ ነው። — ማቴ. 24:14.

7 ሰዎች ከይሖዋና ከሰይጣን ድርጅት አንዱን መምረጥ አለባቸው። ይህ የእያንዳንዳቸውን ሕይወት ይነካል። (ሥራ 26:18) የሰዎችን ትኩረት ወደ ድርጅቱ ለመሳብ ይሖዋ የሰጠንን መልካም መሣሪያዎች ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ትክክለኛውን ምርጫ እንዲያደርጉ ልንረዳቸው እንችላለን። በእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወቅት ይህንን ለማድረግ እቅድ ማውጣት ይኖርብናል። በዚህ መንገድ ከረዳናቸው “በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን ሰላምን፣” አጥብቀው ሊከተሉ ይችላሉ። — 2 ጢሞ. 2:22

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ