ትርጉም ያላቸው ተመላልሶ መጠይቆችን በማድረግ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች እድገት እንዲያደርጉ ማነቃቃት
1 ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ለመርዳት ዘወትር ተመላልሰን በመጠየቅ የማያቋርጥ መንፈሳዊ ምግብ መስጠታችን አስፈላጊ ነው። ተመላልሰን መጠየቃችን የሚያደርጉትን መንፈሳዊ እድገት ደረጃ በደረጃ ያፋጥንላቸዋል። (1 ቆሮ. 3:6–9) ጉብኝታችን ትርጉም ያለው እንዲሆን ከተፈለገ የምንጎበኘውን ሰው በአእምሯችን ይዘን በቅድሚያ መዘጋጀታችን በጣም አስፈላጊ ነው።
2 ትራክት የሰጠናቸውን ሰዎች ተመልሰን ማነጋገር፦ ምናልባት በመጀመሪያ ስናነጋግራቸው ያበረከትነው ሰላም በሰፈነበት የሚለውን ትራክት ሊሆን ይችላል።
ባለፈው ጊዜ የተነጋገርንበትን ነገር በአጭሩ ከከለስን በኋላ እንደሚከተለው ብለን ልንጠይቅ እንቸላለን
◼ “እነዚህን ለውጦች ማን ሊያመጣቸው ይችላል? [ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት] እርስዎም እንዲህ ባለው ሁኔታ ቢኖሩ ደስ እንደሚልዎት ምንም ጥርጥር የለውም። በግለሰብ ደረጃ ይህንን ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?” ከዚያም “እርስዎ ይህንን ሕይወት እንዴት ማግኘት ይችላሉ?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር ያለውን ሃሳብ ልታወያየው ትችላለህ። ሰውየው ፍላጎት ካሳየ ለዘላለም መኖር በተባለው መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን “የአምላክ መንግሥት ዜጋ መሆን” የሚለውን 15ኛ ምዕራፍ አሳየው። በመጀመሪያዎቹ ሁለት አንቀጾች ላይ ካወያየነው በኋላ እንደሚከተለው ብለን ልንጠይቀው እንችላለን:- “ስለ አምላክ መማራችን እንዴት ሊነካን ይገባል?” በሚቀጥለው ጉብኝት ወቅት ለጥያቄው መልስ ለመስጠትና በምዕራፉ ላይም ለመወያየት ዝግጅት ሊደረግ ይችላል።
3 “አምላክ በእርግጥ ስለእኛ ያስባልን?” የተባለውን ብሮሹር አበርክተንላቸው የነበሩትን ሰዎች ተመልሰን ስንጠይቅ እንዲህ ለማለት እንችላለን፦
◼ “ባለፈው መጥቼ በነበረ ጊዜ ዛሬ ከሰው ዘር ፊት ስለተጋረጡት ብዙ ችግሮችና አምላክ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ምን ለማድረግ ቃል እንደገባ ተነጋግረን ነበር። ታዲያ አምላክ እስከ አሁን ድረስ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? ባለፈው ጊዜ በተመለከትነው ብሮሹር በስድስተኛው ክፍል ላይ ለዚህ ጥያቄ አስደሳች መልስ እናገኛለን።” በቅርብ የሚያገኘው ከሆነ የቤቱ ባለቤት የራሱን ቅጂ እንዲያመጣ ጠይቀው። ጥቂት አንቀጾችን ከተወያየን በኋላ እንዲህ ብለን ልንጠይቀው እንችል ይሆናል:- “አምላክ በገባልን ተስፋዎች ለመጠቀም እንድንችል ምን ማድረግ ይፈለግብናል”? በሚቀጥለው ጊዜ ከገጽ 28 እስከ 31 በክፍል 11 ስር የሚገኘውን “አሁን እየተገነባ ያለው የአዲስ ዓለም መሠረት” የሚለውን ነጥብ ልናነሳ እንችላለን።
4 መጽሔት ያበረከትንላቸውን ሰዎች ተመልሰን መጠየቅ፦ የቤቱን ባለቤት ትኩረት የሳበ አንድ የተወሰነ ርዕስ ከመጽሔቱ መርጠህ ከነበረ ተመልሰህ ስትሄድ የምትወያይበትን ሐሳብ በአንድ ቁልፍ ጥቅስና ጥቅሱን በሚያብራሩት ሐሳቦች ላይ በመመሥረት በዚያው ርዕስ ውስጥ በሚገኙ ተጨማሪ ነጥቦች አዳብረው። ፍላጎቱ እየጨመረ ከሄደ የመጽሔቶቹን ጠቃሚነት ማስረዳት ይቻላል። ተከታዩ እትም ተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ይዞ የሚወጣ ከሆነ ትኩረቱን ወደዚያ ማዞርም ይቻላል። አለበለዚያም ትኩረቱን ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ስለ ጉዳዩ ወደሚናገርበት ርዕስ በማዞር በሚቀጥለው ስንመለስ እንድንወያይበት ሁኔታውን ልናመቻች እንችላለን።
5 ሳናቋርጥ ትርጉም ያላቸውን ተመላልሶ መጠይቆች በማድረግ የምናሳየው ግላዊ አሳቢነት ለሰዎችና ለይሖዋ ያለንን ፍቅር ያሳያል። (ዮሐንስ 13:34, 35) አዘውትረን ትርጉም ያላቸውን ተመላልሶ መጠይቆች በማድረግ በክልላችን ውስጥ ያሉት ሰዎች መንፈሳዊ እድገት ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ማነቃቃታችንን እን ቀጥል።