ሰዎች በአምላክ የሰላም መንግሥት ላይ ያላቸውን ፍላጎት አሳድግ
1 በየካቲት ወር በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። ዓላማችን ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ለአምላክ መንግሥትና እርሷ ለምታከናውናቸው ነገሮች ያላቸውን አድናቆት እንዲያሳድጉ መርዳት መሆን ይኖርበታል። ይህንን ለማከናወን የአመለካከት ጥያቄዎች መጠየቃችን ሊረዳን ይችላል።
2 የወዳጅነት ሰላምታ ካቀረብን በኋላ እንደሚከተለው ልንል እንችል ይሆናል፦
◼ “በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ለውጦች እየተካሄዱ ነው፤ ሰላምን የማስፈኑ ዓላማም ብዙውን ጊዜ ይጠቀሳል። እውነተኛ ሰላም ሊገኝ እንደሚችል ይሰማዎታልን? [ሐሳብ እንዲሰጥ ፍቀድለት] ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ሰላም እንዲሰፍን በሰው ልጆች ላይ ተስፋ ቢያደርጉም አምላክ ግን በመዝሙር 46:9 ላይ ሰላምን ለማምጣት እንዴት ቃል እንደገባ ልብ ይበሉ። [አንብበው።] አምላክ የሚወስደው እርምጃ በምድር ላይ ምን ለውጦችን የሚያመጣ ይመስልዎታል። [የቤቱ ባለቤት የሚሰጠውን መልስ አዳምጥና ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት የተባለውን ትራክት አሳየው።] እዚህ ላይ ስዕሉ የሚያሳየው ነገር በዓይነ ሕሊናዎ ሊታይዎት ይችላልን?” “በአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር ያለውን ነጥብ ተወያዩበት። ሁኔታው ከፈቀደልህ ለዘላለም መኖር በተባለው መጽሐፍ ውስጥ ከገጽ 11–13 ወደሚገኘው ተመሳሳይ ነጥብ ትኩረቱን በማዞር መጽሐፉን ለማበርከት ትችል ይሆናል። ተጨማሪ ማብራሪያ ደግሞ ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 227 እስከ 232 ላይ “የአምላክ መንግሥት ምን ታከናውናለች?” በሚለው ርዕስ ስር ልታገኝ ትችላላህ። መጽሐፍ ያበረከትክበት ወይም ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳይ ፍንጭ ያገኘህበትን ቤት ተመልሰህ ለመጎብኘት ዝግጅት አድርግ።
3 ወይም እንዲህ ለማለት እንችል ይሆናል፦
◼ “እያንዳንዳችን በዕለታዊ የኑሮ እንቅስቃሴያችን ስለሚያጋጥሙን ከበድ ያሉ ችግሮች ብዙ ሰዎች የሚሰማቸውን ጭንቀት ይናገራሉ። ከእነዚህ ችግሮች የምንገላገልበት ተስፋ እንደሚኖር ይሰማዎታልን? [አስተያየት እንዲሰጥ ፍቀድለት።] አንዳንዶች ለሚደርስብን መከራ አምላክ ግድ የለውም የሚል ስሜት አላቸው። ይሁን እንጂ በራእይ 21:3, 4 ላይ ምን ተስፋ እንደሰጠ ልብ ይበሉ።” ጥቅሱን አንብበው። ከዚህ በኋላ ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ፣ አንድ በቅርቡ የወጣ መጽሔት ወይም ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን? የተባለው ትራክት ሊበረከት ይችላል። ለዘላለም መኖር የተባለው መጽሐፍ ሲበረከት ከገጽ 156–158 ድረስ እንዲሁም በገጽ 161ና 162 ላይ ያሉት ነጥቦቸና ሥዕላዊ መግለጫዎች ትኩረት ሊሰጥባቸው ይችላል። ይህ ከቤቱ ባለቤት ጋር በምታደርገው ውይይት የአምላክ መንግስት የምታከናውነውን ነገር ለማስረዳት ይረዳሃል። ከዚያ በኋላ የተለመደውን መዋጮ በመቀበል ማበርከት ይቻላል። አምላክ ስለእኛ በእርግጥ ያስባልን? የሚለውን ብሮሹር ካበረከትክ ደግሞ:- “ታዲያ መከራ እንዲኖር ለምን ፈቀደ?” የሚለው ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። በብሮሹሩ ውስጥ የሚገኘውን 6ኛ ክፍል ጠቁመውና በሚቀጥለው ጉብኝትህ ወቅት ለመወያየት ዝግጅት አድርግ።
4 በቅርብ ጊዜ ከወጡት መጽሔቶች መካከል ከአንዱ በመረጥከው ነጥብ ላይ በማተኮር መጽሔት ለማበርከት ትመርጥ ይሆናል።
የቤቱ ባለቤት ፍላጎት እንዳለው ከገለጸ መጽሔቱን እንደሚከተለው በማለት ልታስተዋውቅ ትችል ይሆናል፦
◼ “ይህ እትም በርዕሱ ላይ ጠለቅ ያለ ውይይት ያደርጋል። [ቀደም ብለህ የመረጥከውን አንድ ወይም ሁለት ዓረፍተ ነገር አንብብለት።] ይህ ርዕስ ለእርስዎና ለቤተሰብዎ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ሌሎች ተጨማሪ ሐሳቦችን ይዟል። ስለዚህ ጉዳይ ለማወቅ ፍላጎት ስላለዎት ይህንን እትምና የእርሱ ተጓዳኝ የሆነውን ይህንን መጽሔት ለአስተዋጽኦ __________ አስከፍለን ብንተውልዎ ደስ ይለናል።
5 ዛሬ በሰው ዘር ፊት ለተጋረጡት ችግሮች ሰዎች መልስ ለማግኘት ወደ የት ዞር ማለት እንዳለባቸው በማወቅ ረገድ በአብዛኛው ግራ ተጋብተዋል። የወደፊቱ ጊዜ የያዘውን ብሩሕ ተስፋ ለማካፈል የሚያስችል መብት አግኝተናል። (ሥራ 17:27) እንግዲያው ሰዎች እውነተኛ የሰላም ምንጭ ወደሆነችው ወደ አምላክ መንግሥት ሐሳባቸውን እንዲያዞሩ ተግተን እንርዳቸው።