የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 8—ሩት
ጸሐፊው:- ሳሙኤል
የተጻፈበት ቦታ:- እስራኤል
ተጽፎ ያለቀው:- 1090 ከዘአበ አካባቢ
የሚሸፍነው ጊዜ:- 11 ዓመት የመሳፍንት አገዛዝ
የሩት መጽሐፍ በቦዔዝና በሩት መካከል የነበረውን ውብ የፍቅር ታሪክ የሚገልጽ ማራኪ ድራማ ነው። ሆኖም እንዲሁ ስለ ፍቅር ታሪክ ብቻ የሚያወራ መጽሐፍ አይደለም። መጽሐፉ ሰዎችን ለማዝናናት ተብሎ የተጻፈ አይደለም። መጽሐፉ ይሖዋ የመንግሥት ወራሽ ለማስገኘት ያለውን ዓላማ ጎላ አድርጎ የሚገልጽ ከመሆኑም በላይ ፍቅራዊ ደግነቱን ከፍ አድርጎ ያሳያል። (ሩት 1:8፤ 2:20፤ 3:10) ይሖዋ ቀደም ሲል ካሞሽ የተባለውን አረማዊ አምላክ ታመልክ የነበረችውንና ከዚያም ወደ እውነተኛው ሃይማኖት የተለወጠችውን አንዲትን ሞዓባዊት ሴት መርጦ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ አያት እንድትሆን በማድረግ ተወዳዳሪ ያልተገኘለትን ፍቅሩን በሰፊው አሳይቷል። ከአብርሃም እስከ ኢየሱስ በሚደርሰው የዘር ሐረግ ዝርዝር ውስጥ በስም ከተጠቀሱት አራት ሴቶች መካከል አንዷ ሩት ነች። (ማቴ. 1:3, 5, 16) ሩት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በስማቸው ከተሰየሙላቸው ሁለት ሴቶች (ከአስቴር ጋር ማለት ነው) አንዷ ናት።
2 የሩት መጽሐፍ “መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ . . .” በሚሉት ቃላት በመጀመር ስሜት ቀስቃሽ ትረካውን ይቀጥላል። ከእነዚህ ቃላት ለመረዳት እንደሚቻለው መጽሐፉ የተጻፈው ከጊዜ በኋላ ማለትም በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ነው። ይሁን እንጂ በመጽሐፉ ውስጥ የተመዘገቡት ክንውኖች የመሳፍንትን የ11 ዓመት ጊዜ ይሸፍናሉ። ምንም እንኳ ጸሐፊው በስም ባይጠቀስም የመሳፍንትን መጽሐፍ የጻፈው በነገሥታት ዘመን መግቢያ ላይ በታማኝነቱ ጉልህ ሥፍራ የነበረው ሳሙኤል ሳይሆን አይቀርም። የመደምደሚያዎቹ ቁጥሮች ዳዊት ጉልህ ሥፍራ እየያዘ እንደመጣ መጠቆማቸው መጽሐፉ የተጻፈበትን ጊዜ 1090 ከዘአበ ገደማ ያደርገዋል። ይሖዋ ከይሁዳ ነገድ ‘አንበሳ’ እንደሚያስነሳ ቃል መግባቱን ጠንቅቆ የሚያውቀውና ከዚያው ከይሁዳ ነገድ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን እንዲቀባ ይሖዋ የተጠቀመበት ሳሙኤል እስከ ዳዊት የሚደርሰውን የዘር ሐረግ ለመመዝገብ ጥልቅ ፍላጎት እንደሚኖረው የታወቀ ነው።—ዘፍ. 49:9, 10፤ 1 ሳሙ. 16:1, 13፤ ሩት 1:1፤ 2:4፤ 4:13, 18-22
3 የሩት መጽሐፍ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንም ጥያቄ ተነስቶ አያውቅም። ይሖዋ በማቴዎስ 1:5 ላይ የኢየሱስ የትውልድ ሐረግ ሲዘረዘር የሩትም ስም እንዲጠቀስ ማድረጉ መጽሐፉ ትክክለኛ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ነው። አይሁዳውያን የሩትን መጽሐፍ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ክፍል እንደሆነ አድርገው ያልተቀበሉበት ጊዜ የለም። የመጽሐፉ ቁርጥራጮች ከ1947 ጀምሮ በተገኙት የሙት ባሕር ጥቅሎች ውስጥ ከሌሎች የቅዱሳን ጽሑፎች ክፍል ጋር አብረው መገኘታቸው ምንም አያስደንቅም። ከዚህም በላይ የሩት መጽሐፍ ከይሖዋ የመንግሥት ዓላማ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚስማማ ከመሆኑም በላይ የሙሴ ሕግ የሚጠይቃቸውን ብቃቶች ሁሉ ያሟላል። ምንም እንኳ ጣዖት አምላኪ ከሆኑት ከነዓናውያንና ሞዓባውያን ጋር ጋብቻ መመሥረት ለእስራኤላውያን የተከለከለ ቢሆንም የይሖዋን አምልኮ እንደተቀበለችው እንደ ሩት ካሉ የባዕድ አገር ሰዎች ጋር መጋባትን ግን የሚከለክል አልነበረም። መልሶ ስለ መቤዠትና የወንድምን ሚስት ስለማግባት የሚናገረው የሙሴ ሕግ በሩት መጽሐፍ ውስጥ አንድ በአንድ ተከብሯል።—ዘዳ. 7:1-4፤ 23:3, 4፤ 25:5-10
ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት
9 ይህ አስደሳች ዘገባ ጽድቅን የሚያፈቅሩ ሰዎች ጠንካራ እምነት እንዲገነቡ ስለሚረዳቸው ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛል። በዚህ አስደሳች ድራማ ውስጥ ተካፋይ የሆኑት ሰዎች ሁሉ በይሖዋ ላይ ድንቅ እምነት እንዳላቸው ያሳዩ ሲሆን ‘በእምነታቸውም ተመስክሮላቸዋል።’ (ዕብ. 11:39) በዛሬው ጊዜ ለምንኖረው ለእኛም ጥሩ ምሳሌ ይሆኑናል። ኑኃሚን በይሖዋ ፍቅራዊ ደግነት ላይ ጥልቅ የሆነ ትምክህት እንዳላት አሳይታለች። (ሩት 1:8፤ 2:20) ሩት የይሖዋን አምልኮ ለመከታተል ስትል የተወለደችበትን አገር በፈቃዷ ለቅቃ ወጥታለች። ታማኝና ታዛዥ እንዲሁም ፈቃደኛ ሠራተኛ መሆኗን አስመስክራለች። ቦዔዝ ለይሖዋ ሕግ የነበረው ልባዊ አድናቆትና የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የነበረው የትሕትና መንፈስ እንዲሁም ለታማኝዋ ኑኃሚንና ለታታሪዋ ሩት የነበረው ፍቅር በመቤዠት ሥርዓት የማግባት መብቱን እንዲጠቀምበት አድርጎታል።
10 ይሖዋ ለጋብቻ ያወጣው ዝግጅትና በዚህ ወቅት ደግሞ በመቤዠት ሥርዓት የሚደረገው ጋብቻ ለእርሱ ክብር በሚያመጣ መንገድ ተሠርቶበታል። ቦዔዝና ሩት እንዲጋቡ ሁኔታዎችን ያመቻቸው ይሖዋ ሲሆን በፍቅራዊ ደግነቱም ባርኳቸዋል። ወደ ዳዊት ከዚያም አልፎ ወደ ታላቁ ዳዊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያደርሰው ንጉሣዊ መሥመር ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ጠብቆ ለማቆየት ተጠቅሞበታል። ይሖዋ ባወጣው ሕጋዊ ደንብ መሠረት የመንግሥቱ ወራሽ የሚገኝበትን መሥመር በጥንቃቄ መከታተሉ የመንግሥቱ ተስፋዎች ወደፊት ሙሉ ፍጻሜያቸውን እንደሚያገኙ ያለን እርግጠኝነት እንዲጠናከርና ወደፊትም በልበ ሙሉነት አሻግረን እንድንመለከት ሊያደርገን ይገባል። ‘ከክንፎቹ በታች መጠጊያ እንድናገኝ ያደረገውና’ በመንግሥቱ አማካኝነት ታላቅ ፍጻሜያቸውን ለማግኘት ወደፊት በመገስገስ ላይ ያሉ ተስፋዎችን የሰጠን የመንፈሳዊ እስራኤል አምላክ ይሖዋ ፍጹም ደሞዛችንን እንደሚሰጠን በመተማመን በዘመናችን እየተከናወነ ባለው የመከር ሥራ እንድንጠመድ ሊያነሳሳን ይገባል። (2:12) ከዚህ መንግሥት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው ከሌሎች ዘገባዎች መካከል የሩት መጽሐፍም ይገኝበታል።