የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/00 ገጽ 4
  • የይሖዋን ትዕግሥት ታደንቃላችሁን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋን ትዕግሥት ታደንቃላችሁን?
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የይሖዋን ትዕግሥት ኮርጁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ይሖዋና ኢየሱስ ካሳዩት ትዕግሥት ትምህርት ማግኘት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ትዕግሥት ማሳየታችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • በአገልግሎታችን ትዕግሥተኛ መሆን ይገባናል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
km 7/00 ገጽ 4

የይሖዋን ትዕግሥት ታደንቃላችሁን?

1 ይሖዋ ላለፉት 10፣ 20 እና ከዚያም ለሚበልጡ ዓመታት ተጨማሪ ምስክርነት እንዲሰጥ ባይፈቅድ ኖሮ እውነትን መማር ትችሉ ነበር? ይሖዋ ብዙ ቁጥር ያላቸው ተጨማሪ ሰዎች “ወደ ንስሐ እንዲደርሱ” በመፍቀዱ ምን ያህል አመስጋኞች ነን። ይሁን እንጂ የይሖዋ ታላቅ የፍርድ ቀን “እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል።” (2 ጴ⁠ጥ. 3:​9, 10) በመሆኑም የአምላክ ትዕግሥት ይህንን የነገሮች ሥርዓት ወደ መጨረሻው ከማምጣት እንደዘገየ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባውም።​—⁠ዕን. 2:​3

2 ለሰዎች እዘኑላቸው:- የይሖዋ ትዕግሥት እኛ ልንረዳው ከምንችለው በላይ ስለሆነ ዓላማውን መሳት አይኖርብንም። (ዮናስ 4:​1-4, 11) ይሖዋ የሰው ዘር የሚገኝበትን አሳዛኝ ሁኔታ ስለሚመለከት ለሰዎች ይራራላቸዋል። ኢየሱስም ተመሳሳይ ስሜት ያለው ሲሆን ይሰብክላቸው ለነበሩት ሰዎች በማዘን የወንጌላዊነቱ ሥራ እንዲስፋፋና ተጨማሪ ሰዎች የዘላለም ሕይወት የማግኘት አጋጣሚ እንዲኖራቸው ይፈልግ ነበር።​—⁠ማቴ. 9:​35-38

3 አሳዛኝ የሆኑ ነገሮች ወይም አደጋዎች ሲደርሱ ልባችን እውነትን ላላወቁት ሰዎች አያዝንምን? በዛሬው ጊዜ በዓለም ውስጥ ያለውን ዝብርቅ ለመቋቋምና ከበስተኋላው ያለውን ትርጉም ለመረዳት እየሞከሩ ያሉት ሰዎች “እረኛ እንደሌላቸው በጎች” ናቸው። (ማር. 6:​34) ምሥራቹን በቅንዓት በመስበክ ጥሩ የልብ ዝንባሌ ያላቸውን ሰዎች እናጽናናለን እንዲሁም ለይሖዋ ትዕግሥት ያለንን አድናቆት እናሳያለን።​—⁠ሥራ 13:​48

4 ሥራችን አጣዳፊ ነው:- ባለፈው ዓመት 323, 439 ሰዎች የተጠመቁ ሲሆን ከ14, 000, 000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በመታሰቢያው በዓል ላይ ተገኝተዋል። ይህ ከዚህ ክፉ ሥርዓት ጥፋት ለማምለጥ የሚያስችል ግሩም አጋጣሚ ያላቸው ብዙ ተጨማሪ ሰዎች እንዳሉ የሚያሳይ ነው! ‘የእጅግ ብዙ ሰዎች’ ጠቅላላ ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ አናውቅም። (ራእይ 7:​9) እንድንሰብክ የተሰጠን ትእዛዝ መቼ እንደሚያበቃም አናውቅም። ይሖዋ ግን ያውቃል። በመሆኑም ምሥራቹ እሱ እስከሚፈልገው ድረስ ከተሰበከ በኋላ “መጨረሻው ይመጣል።”​—⁠ማቴ. 24:​14

5 የቀረው ጊዜ ጥቂት ሲሆን የአምላክ ቀን በእጅጉ ተቃርቧል። (1 ቆ⁠ሮ. 7:​29ሀ፤ ዕብ. 10:​37) አለምንም ጥርጥር “ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአል።” (ሮሜ 13:​11) የመለኮታዊውን ትዕግሥት ዓላማ አንሳት። ከዚህ ይልቅ የጽድቅ ፍቅር ያላቸው ተጨማሪ ሰዎች የይሖዋን ታላቅ ምሕረት እንዲያገኙ በጥድፊያ ስሜት እንስበክ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ