ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ኅሣሥ 26, 2005 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ በቃል መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከኅዳር 7 እስከ ታኅሣሥ 26, 2005 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-7ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. ምክር የምንሰጠው “በፍቅር” እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርብናል? (ፊል. 9) [be ገጽ 266]
2. “ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት” በመጠቀም ምክር መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? (ቲቶ 1:9 የ1954 ትርጉም) [be ገጽ 267 አን. 1-2]
3. በጉባኤ የምናቀርባቸው ንግግሮች የሚያበረታቱ መሆን ያለባቸው ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 268 አን. 1-3፣ ሣጥን]
4. የሙሴን አርዓያ በመከተል፣ ወንድሞች ይሖዋ ለሕዝቦቹ ያደረገውን መለስ ብለው እንዲያስታውሱ መርዳታችን ሊያበረታታቸው የሚችለው እንዴት ነው? (ዘዳ. 3:28፤ 31:1-8) [be ገጽ 268 አን. 5 እስከ ገጽ 269 አን. 1]
5. ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ እያከናወናቸው ባሉት ነገሮችና ወደፊትም በሚያከናውናቸው ነገሮች እንደምንደሰት በሚያሳይ መንገድ መናገራችን አድማጮቻችንን የሚያበረታታቸው ለምንድን ነው? [be ገጽ 269-271]
ክፍል ቁጥር 1
6. የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም (ሴፕቱጀንት) ምንድን ነው? የክርስቲያኖችን ትኩረት የሚስበውስ ለምንድን ነው? [si ገጽ 307 አን. 12 እስከ ገጽ 310 አን. 14]
7. ማሶሪታውያን እነማን ነበሩ? በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ረገድስ ምን የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል? [si ገጽ 310 አን. 18፤ ገጽ 311 አን. 20-21]
8. የእንግሊዝኛው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የዕብራይስጡ ክፍል በዋነኝነት መሠረት ያደረገው የትኛውን ቅጂ ነው? ይህ ትርጉም ትክክለኛና አስተማማኝ ነው ሊባል የሚችለውስ ለምንድን ነው? [si ገጽ 312 አን. 28, 30]
9. የጥንቶቹ ክርስቲያኖች የአምላክን ቃል ለማወጅ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበራቸው ያሳዩት እንዴት ነው? [si ገጽ 315 አን. 1-5]
10. አሁን በእጅ በሚገኙ የቅዱሳን ጽሑፎች ግልባጮችና የተጣሩ ቅጂዎች ላይ የሚደረግ ጥናት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያሳውቀናል? [si ገጽ 320 አን. 32]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ዳዊት ቤተ መቅደሱን እንዲገነባ አለመፈቀዱ እርሱ ባካሄዳቸው ጦርነቶች ይሖዋ አለመስማማቱን የሚያሳይ ነው? (1 ዜና 22:6-10)
12. ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለይሖዋ አምልኮ በወሰነበት ወቅት ባቀረበው ጸሎት ላይ፣ ይሖዋ የአገልጋዮቹን ፍላጎት የሚያሟላው በቡድን ደረጃ ብቻ እንዳልሆነና እርሱን የሚፈራውን የእያንዳንዱን ግለሰብ ሁኔታ እንደሚያውቅ የገለጸው እንዴት ነው? (2 ዜና 6:29, 30) [w97 4/15 ገጽ 4]
13. በ2 ዜና መዋዕል 20:17 ላይ በሚገኘው ሐሳብ መሠረት የማጎጉ ጎግ በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ጊዜ ምን ማድረግ ይኖርብናል?
14. የባኦስ የንግሥና ዘመን የጀመረው “አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት” ከሆነና ግዛቱም የቆየው ለ24 ዓመታት ብቻ ከሆነ፣ “አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት” ባኦስ “በይሁዳ ላይ” እንዴት ሊዘምት ይችላል? (1 ነገ. 15:33፤ 2 ዜና 16:1)
15. ሁለተኛ ዜና መዋዕል 20:22, 23 የሰይጣን ዓለም በቅርቡ ምን እንደሚያጋጥመው ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው እንዴት ነው? [w84 7/1 ገጽ 18 አን. 17 (7-105 ገጽ 10 አን. 17)]