የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ታኅሣሥ 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 12 (32)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆኑ) የጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 2005 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችንም መጠቀም ይቻላል። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ በመግቢያችን ላይ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንዴት በቀላሉ መጠቀም እንደሚቻል ሐሳብ ስጥ።
15 ደቂቃ:- “ለተግባር የሚያነሳሳን ትምህርት ቤት።” በትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በንግግር የሚቀርብ። ከጥቅምት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ።
20 ደቂቃ:- “ሕይወት የሚያስገኝ ትምህርት።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከመለኮታዊ ትምህርት ያገኙትን ጥቅም እንዲናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ።
መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 69 (160)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “አቀራረብን በመለዋወጥ ለሰዎች ልባዊ አሳቢነት አሳዩ።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። አንድ አስፋፊ የቤቱ ባለቤት የሚሰጠውን መልስ መሠረት በማድረግ አቀራረቡን ከዚያ ጋር ሲያስማማ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
25 ደቂቃ:- “ልጃችሁ ከባድ ውሳኔ የማድረግ ችሎታ አለው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ክፍሉን የሚያቀርበው የጉባኤ ሽማግሌ ይሆናል። ጥሩ የንባብ ችሎታ ያለው ወንድም አንቀጾቹን እንዲያነብልህ አድርግ። ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን ጥቅሶች ተወያዩባቸው። አንቀጽ ሁለትን ከተወያያችሁበት በኋላ በሰኔ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 16-17 [ሣጥኑን ጨምሮ] አንቀጽ 16-17 ላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን ወጣቶች ሁኔታ አነጻጽር። ክፍሉን ስትደመድም ወላጆች ከመጠበቂያ ግንቡ ላይ ርዕሱን በሙሉ እንዲከልሱ እንዲሁም ልጆቻቸው እምነታቸውን በእርግጠኝነት መግለጽ እንዲችሉ ለማሠልጠን መጽሐፍ ቅዱስ ደምን አስመልክቶ የሚሰጠውን መመሪያ ከልጆቻቸው ጋር የሚወያዩበትና የሚለማመዱበት ፕሮግራም በማውጣት በክፍሉ ላይ የቀረበውን ሐሳብ ወዲያውኑ በተግባር እንዲያውሉ አበረታታቸው። የቤተሰብ ራሶች እያንዳንዱ የተጠመቀ ልጅ የሕክምና መመሪያ ካርድ፣ ያልተጠመቁት ደግሞ የመታወቂያ ካርድ መያዛቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። አንድ ክርስቲያን ሆስፒታል ቢገባና የደም ጥያቄ ቢነሳ ሽማግሌዎች ከአካባቢው የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴ እርዳታ ለማግኘት መጠየቅ ይኖርባቸዋል።
መዝሙር 26 (56) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 38 (85)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የታኅሣሥ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። ጉባኤያችሁ በአዲሱ ዓመት ስብሰባ የሚያደርግበትን ሰዓት የሚቀይር ከሆነ አዲሱን ሰዓት ተናገር። በጥር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ተናገር፤ የመግቢያ ሐሳቦች የት እንደሚገኙም ጠቁም። በገጽ 6 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በመጠቀም (ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ ከሆነ) የጥቅምት 15 መጠበቂያ ግንብ ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መግቢያዎችን መጠቀም ይቻላል።
15 ደቂቃ:- ትሕትናን ልበሱ። በመስከረም 2003 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
20 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 100 (222) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥር 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 35 (79)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- “መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንን በሚገባ እንጠቀምባቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። ከመስከረም 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 ላይ ተጨማሪ ሐሳቦች አክል።
8 ደቂቃ:- የወረዳና የልዩ ስብሰባዎችን ለመከለስ የተደረገ አዲስ ዝግጅት። ከመስከረም 2004 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስ። ወደፊት የምናደርጋቸውን የወረዳ ስብሰባና የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራሞችን ለመከለስ የሚረዱ ጥያቄዎች በመስከረምና በጥቅምት 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ወጥተዋል። ሁለቱ ስብሰባዎች የሚደረጉባቸውን ቀናት ተናገር፤ ማስታወሻ እንዲይዙም አበረታታቸው።
17 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት።