የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/08 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መጋቢት 10 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 17 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 24 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 31 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 3/08 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

መጋቢት 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 65 (152)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 6 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2008 ንቁ! መጽሔቶች ከመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት ጋር ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ የምንገኘው ለምንድን ነው? በግንቦት 15, 2007 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 11-13 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አድማጮች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ በመገኘታቸው እንዴት ጥቅም እንዳገኙ እንዲሁም ዘወትር በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ሲሉ አንዳንድ መሰናክሎችን እንዴት ማሸነፍ እንደቻሉ እንዲናገሩ ጋብዝ።

15 ደቂቃ:- “ሁላችንም ለይሖዋ መስጠት የምንችለው ነገር አለን።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 4 (8)

መጋቢት 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 61 (144)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አድማጮች በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለምንወስደው ክፍል የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2008 ንቁ! መጽሔቶችን ይዘው እንዲመጡ እንዲሁም ለክልላችሁ ተስማሚ የሆኑ መግቢያዎችን እንዲዘጋጁ ንገራቸው። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በጉባኤ ሽማግሌ የሚቀርብ። አንቀጾቹን አንድ በአንድ እያነበብክ አብራራ።

20 ደቂቃ:- “በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙትን ሰዎች እንዴት መርዳት እንችላለን?”* አንቀጽ 5ን ስትወያዩ በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኘን ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 14 (34)

መጋቢት 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53 (130)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ።

15 ደቂቃ:- ወቅታዊ መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2008 ንቁ! መጽሔቶችን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነና ለምን እንዲህ እንዳሉ አድማጮችን ጠይቅ። አድማጮች በአገልግሎት ላይ ሊያስተዋውቁት ካሰቡት ርዕስ ውስጥ ማራኪ ሆነው ያገኟቸውን አንዳንድ ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄ መጠቀም ይቻላል? ከዚያስ በርዕሱ ውስጥ ያለ የትኛው ጥቅስ ቢነበብ ጥሩ ነው? አድማጮች የሰጧቸውን ሐሳቦች በመጠቀም የየካቲት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የየካቲት 2008 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- መልካም ዜና እናበስራለን። አንድ የጉባኤ ሽማግሌ አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገረ በኋላ በሐምሌ 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-19፣ ከአንቀጽ 10-14 ላይ ተመሥርቶ በንግግር ያቀርበዋል። አድማጮች የመንግሥቱን መልእክት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰሙ ማጽናኛና ተስፋ ያገኙት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 11 (29)

መጋቢት 31 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 27 (57)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመጋቢት ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።

20 ደቂቃ:- የ2008ን የዓመት መጽሐፍ በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙበት። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በገጽ 3 ላይ የሚገኘውን “ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ” የሚለውን ተወያዩበት። ሁለት ወይም ሦስት አድማጮች ከዓመት መጽሐፉ ላይ በተለይ ለእነሱ አበረታች ሆኖ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ አድርግ። የዓመት መጽሐፉን በግላቸው ለማንበብ እንዴት ፕሮግራም እንዳወጡ የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ። ሁሉም መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር እንዲያነቡ በማበረታታት ክፍሉን ደምድም።

15 ደቂቃ:- “በአገልግሎት ላይ ስትሆኑ እርስ በርሳችሁ ተናነጹ።”*

መዝሙር 58 (138)

ሚያዝያ 7 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 7 (19)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- ከመጠመቅ ወደኋላ የምትለው ለምንድን ነው? በሐምሌ 1, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-30 ከአንቀጽ 14-17 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ እያሉ ለተጠመቁ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። በወጣትነት ዕድሜያቸው ይህን ትልቅ እርምጃ ለመውሰድ ያነሳሳቸው ምንድን ነው? መጠመቃቸው ጥበቃ ወደሚያስገኝላቸው መንፈሳዊ ጉልምስና እንዲያድጉ የረዳቸው እንዴት ነው?

15 ደቂቃ:- መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት በቀጥታ ጥያቄ አቅርባችሁ ታውቃላችሁ? በጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ገጽ 6 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በአባሪው ላይ በቀረቡት የናሙና መግቢያዎች ላይ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ጥናት ለማስጀመር በእነዚህ መግቢያዎች ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎችን አድርጎ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ተወያዩ። ከዚያም አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አድማጮች በቀጣዩ ሳምንት ውስጥ በቀጥታ ጥያቄ በማቅረብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ጥናት ለማስጀመር ቢያንስ አንድ ጊዜ ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ።

መዝሙር 49 (114)

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ